1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባህላዊ የሽምግልና እና የዳኝነት ስርአት

እሑድ፣ የካቲት 16 2000

ግጭት የህልዉና መሰረት እንደሆነ ያዉቃሉን? አልፎ አልፎ እንደዉም ጥል የሌለዉ ፍቅር፣ ፍቅር አይባልም ይባላል። በአንድ ህብረተሰብ ዉስጥ ጥል ወይም ግጭት የሚፈጠረዉ በህብረተሰቡ ዘንድ ባለ ባህል ወይም ልማድ ምክንያት መሆኑን አዋቂዎች ይናገራሉ

https://p.dw.com/p/E0ln
ምስል picture-alliance/dpa

ሟርትና መተት በአገራችን አንዳንድ ሰዎች በማመናቸዉ ብቻ ከሌሎች ሰዎች ሲጋጩ ይታያል። ለምሳሌ አንዲት ድመት ወይም ወፍ አንድ ሰዉዪ ደጃፍ ላይ የሞተች አይጥ ጥላ በመሄድዋ የቤቱ ባለቤት እገሌ መተት አድርጎበኛል በሚል ከሚጠረጥሩት ግለሰብ ጋር ያለ ምክንያት ተጣሉ አሉ! በተለይ በአፍሪቃችን ዉስጥ የሚከሰቱ ግጭቶች በባህል በልማድ በመሆናቸዉ በዚያዉ በባህል በልማድ የመፍትሄም የዳኝነት መንገድ እንደሚያገኙ ህብረተሰብ ጥናት አዋቂዎች ይገልጻሉ። በአገራችን በሰባት ቤት ጉራጌ ዘንድ ያለዉን የግጭት መፍቻ ዘዴ፣ የሽምግልና ባህል ላይ ጥናት ያደረጉት አቶ ወንደሰን አዉላቸዉ ያጫዉቱናል መልካም ቆይታ