1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባህርና ብዝሃ ህይወት

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 7 2001

አሶችን ከልማዳዊዉ ዘዴ አልፎ ደማሚት እያፈነዱ ማስገሩ ዉሃዉን ከመመረዝ ባሻገር የዉሃ ዉስጥ ቅሪት አካላትን ሁሉ እየጎዳ ነዉ።

https://p.dw.com/p/GHMw
የጃካርታ አሳ ገበያ
የጃካርታ አሳ ገበያምስል AP

የባህር ፍጥረታትን አላግባብ ማጥመዱ ብዝሃ ህይወትን እያመናመነ ሄዷል። አሳን መመገብ ለጤና መልካምነቱ ሲነገር መስማቱ አዲስ አይደለም። አሳን መብላት በብልሃት ደግሞ የእኛ ወገኖች ምሳሌ ነዉ። ስለአሳ ምግብነትና አመጋገብ ሳይሆን አሳን ያለአግባብ ማጥመድ እያስከስላዉ ችግር እንመለከታለን። ለነገሩ አሳ ብቻ አይደለም ከባህር እንስሳት ለምግብነት የሚዉለዉ። እኛ በተለይ እንኳን ባህር አልባ ሆነን ቀርቶ ድሮም የማንቀምሳቸዉ በርካታ ሌሎች ግን ነፍሳቸዉን ቢሰጡ እንኳን የማይሳሱላቸዉ የባህር ዉስጥ እንስሳት ለምግብነት ይዉላሉ።