1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባርነት በሀያ አንደኛው ክፍለ ዘመን

ሰኞ፣ ሐምሌ 13 2001

በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በተለይም በሰለጠነው ዓለም ባርነት አገዛዝ ቀርቷል ተብሎ ነው የሚታመነው ። ይሁንና በአሁኑ ዘመንም ጀርመንን ጨምሮ በእዳንድ የአውሮፓ ሀገራት ጭምር ሰዎችን ከልክ በላይ በማሰራት አለአግባብ የሚበዘብዙ እና እንደ ባሪያ የሚይዙ እንዳሉ በተለያዩ አጋጣሚዎች ተደርሶበታል ።

https://p.dw.com/p/ItNG
ምስል picture-alliance/dpa

በተለይ በቤት ሰራተኝነት በሆቴል ቤቶች በምግብ አብሳይነት እንዲሁም በግንባታ ስራ ላይ የተሰማሩ አንዳንድ የውጭ ዜጎች መብታቸውን ባለማወቅ እንደሚበዘበዙ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በሚያወጧቸው አንዳንድ ዘገባዎች ላይ ተመልክቷል ። ይህን መሰሉን ድርጊት የሚከታተለው የጀርመን የስብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት የጉልበት ብዝበዛውን ለመከላከል ልዩ ልዩ ጥረቶችን ከማድረጉም በላይ የችግሩን ሰለባዎችም እየረዳ ነው ። እዚህ ጀርመን ውስጥ በትውልደ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ጀርመናዊ በሆኑ ግለሰብ የኢትዮጵያ ምግብ ቤት ውስጥ በምግብ አብሳይነት ሲያገለግሉ የቆዩት አንዲት ኢትዮጵያዊት ከአሰሪያቸውዋ ይሰጣቸው በነበረው አነስተኛ ክፍያ እና ደረሰብኝ ባሉት የስራ በደል መንስኤ በዚህ ድርጅት ዕርዳታ ከሰው ተፈርዶላቸዋል ። ልደት አበበ በጀርመን በዚህ መልኩ የሚፈፀም ብዝበዛን ለመከላከል የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶችን ተግባርና የኢትዮጵያዊቷን ጉዳይ የተመለከተ ዘገባ አጠናቅራለች ።

ልደት አበበ ፣ ሂሩት መለሰ