1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቤተልሔም አለሙ እና «ሶል ሬብልስ»

ዓርብ፣ መስከረም 18 2005

ጫማዎቿ ከ 50 በላይ በሚሆኑ ሀገሮች ለገበያ ቀርበዋል። ያረጁ የመኪና ጎማዎችን ዳግም በጥቅም ላይ በማዋል የተለያዩ ጫማዎች የሚመረትበት ፋብሪካ አቋቁማለች።- ቤተልሔም አለሙ።

https://p.dw.com/p/16GUH
Ein Schusterhammer neben einem Herrenschuh in die Meisterwerkstätte von Florian Henke in Pullach, aufgenommen 2005. Foto: Heinz von Heydenaber +++(c) dpa - Report+++
ምስል picture-alliance/dpa

«ሶል ሬብልስ» በመባል የሚታወቀው የጫማ ውጤቶች ባለቤት - ቤተልሔም አለሙ ፤ባለትዳር እና የ 3 ልጆች እናት ናት። ከሰባት አመት በፊት ነበር በአዲስ አበባ የጫማ ፋብሪካ የከፈተችው። ዛሬ ይኼው ድርጅት አድጎ ከመኪና ጎማ የስኒከር ጫማ ሶሎች፤ ጫማዎች እና ነጠላ ጫማዎች ሌሎች ሌሎችንም ያመርታል። ቤተልሔም የስኬቷን ምስጢር አካፍላናለች። ፋብሪካው አሁን ከደረሰበት ደረጃ ለማድረስ የቻለችው በግሏ ጥረት ብቻ እንደሆነ ቤተልሔም ትናገራለች።

የ32 አመቷ ቤተልሔም ይህንን ስራ ስትጀምር አምስት ሠራተኞች ብቻ ነበሯት። ዛሬ አምራች እና አከፋፋዮቹን ጨምሮ ወደ 300 ደርሰዋል። ቤተልሔም ንግዷን ብቻ ሳይሆን የሌሎች ኢትዮጵያውያንን ኑሮ መለወጥም ሌላው አላማዬነው ትላለች። ለሠራተኞች ጥሩ ክፍያ መስጠት ብቻ ሳይሆን አካል ጉዳተኞችንም በሥራው አለም ፋብሪካው ያሳትፋል።

በአለም አቀፍ ደረጃ አምራቾች በተሠማሩበት ዘርፍ የሚገባቸውን ክፍያ አግኝተው እንዲሠሩ እና ምርቶች የተፈጥሮ ይዞታቸዉ ሳይለወጥ ለአካባቢያችን ተስማሚ በሆነ መንገድ እንዲመረቱ በሚሟገተው « WORLD FAIR TRADE ORGANISATION ዘንድ የሶል ሬብልስ ውጤቶች እውቅና አግኝተዋል። ነጠላ ጫማዎች፣ ጫማ ማሰሪያዎች፣ ቡትስ ጫማዎች እና ሌላም ሌላም በፋብሪካው ዘመናዊ እና ደማቅ ቀለማት ይዘው ይመረታሉ።

ከቤተልሔም አለሙ ጋ ያደረግነውን ቆይታ ከዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ