1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቤተክህነት እና የማንበብ ባህል

እሑድ፣ ኅዳር 6 2002

ቤተ ክህነት በኢትዮጽያችን ለስነ-ጽሁፍ እድገት መሰረቱን የጣለች በኻላም በርካታ ሊቃዉንት በቤተክህነቱ ጀምረዉ አሉ ወይም አለን የምንላቸዉን የድርሰት ስራዎች ለወገን ያበረከቱት ጥልቅ አንባብያን በመሆናቸዉ ነዉ።

https://p.dw.com/p/KX98
ምስል picture alliance/dpa

ለምሳሌ ቆየት ካሉት ኢትዮጽያዉያን ደራሴዎች መካከል አዲስ አለማየሁ፣ አቤ ጉበኛ፣ ተመስገን ገብሪ፣ ጥልቅ አንባብያን እና ታዋቂ ደራሲ ከምንላቸዉ መካከል ጥቂቶቹ ናቸዉ፣ ሲሉ በኢትዮጽያ የፕሪስ ድርጅት የህግ አገልግሎት ሃላፊ የሆኑት አቶ አበረ አዳሙ ባለፈዉ ሳምንት ጥንቅራችን ላይ መግለጻቸዉ ይታወሳል። በኢትዮጽያ ደራስያን ማህበር ምክትል ፕሪዝደንት አቶ ደረጀ ገብሪም የማንበብ ባህል ጥንታዊነትን ሳይገልጹ አላለፉም፣ ከመጠምጠም መማር ይቅደም ያሉን እነዚህ ምሁራን ዛሪ ደግሞ የሰዉ ጌጥ አያደምቅ ይሉናል፣ በአገራችን ደራስያን የሚቀርቡትን መጻህፍት አገራችንን ባህላችንን የሚያስተዋዉቀንን መጽሃፍ መጀመር አለብን ይሉናል። ከጥንቅሩ ጋር አዜብ ታደሰ ነኝ መልካም ቆይታ

እኛ ኢትዮጽያዉያን በስብሰባም ላይ ሆነ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ስለአዋቂዎች ስንጠቅስ መጀመርያ በበለጸጉት አገራት ያሉትን ደራሲዎች ወይም ሊቃዉንቶች በመጥቀስ ነዉ ንግግራችንን የምንጀምረዉ ወይም የምንዘጋዉ ያሉን አቶ አበረ አዳሙ የአገራችን ሊቃዉንቶች የጻፉትን ያሉትን ለማወቅ የማንበብን ባህል ማጠናከር አለብን ብለዋል። የማይካደዉ ግን የማንበብ ባህል ባገራችን ጥንታዊ ነዉ!
«የምዕራባዉያንን የማንበብ ባህል አይተን ብዙዎቻችን ኢትዮጽያዉያን የማንበብ ባህል የለንም ብለን የደመደምን ጥቂቶች አይደለንም። በኢትዮጽያ በድርሰት አለም በመጸሃፍ አለም ያሉ ምሁራን ደግሞ ትልቅ ስህተት መሆኑን በማስረገጥ ይገልጻሉ። ከኢትዮጽያ ደራስያን ማህበር ምክትል ሊቀመንበር ከአቶ ደረጀ ገብሪና በኢትዮጽያ ፕሪስ ድርጅት የህግ ክፍል ዋና ሃላፊ ከሆኑት ከአቶ አበረ አዳሙ ጋር ዉይይት አድርገናል ያድምጡ

አዜብ ታደሰ