1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አቋማቸው

ረቡዕ፣ መጋቢት 9 2001

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት ወይም በኢጣልያውያኑ እንደሚጠሩዋቸው ቤኔዲቶስ አስራ ስድስተኛው ሁለት የአፍሪቃ ሀገሮችን ለመጎብኘት ትናንት ካሜሩን መዲና ያውንዴ ገብተዋል።

https://p.dw.com/p/HEzV
ምስል AP

ሌላዋ የሚጎበኙዋት ሀገር አንጎላ ስትሆን፡ መንፈሳዊው መሪ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከሆኑ ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ አፍሪቃን ሲጎበኙ ይህ የመጀመሪያቸው ነው። በጉዞ ላይ እንዳሉ ካጀቡዋቸው ጋዜጠኞች በኤድስና በኮንዶም አጠቃቀም ዙርያ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት፡ አዲስ ያልሆነው መልሳቸው አንዳንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችን ቅር ማሰኘቱ አልቀረም።

ተኽለእዝጊ ገብረየሱስ
አርያም አብርሀ

ሸዋዬ ለገሠ