1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ብሄራዊ ድግስ በጎንደር

ሐሙስ፣ ጥር 12 2003

እንኳን ለጥምቀት በአል አደረሳችሁ! አድማጮች ወረሃ ጥር በአገራችን በተለይ የጥምቀትን በአል በማማስታከክ ቤተሰብ የሚገኛኝበት አገር ቀዪ የሚጎበኝበት መሆኑ ይታወቃል።

https://p.dw.com/p/Qtlr
ምስል CC/Mark Abel

ዘንድሮ በተለይ የጎንደር ከተማ ባህላችንን ወጋችንን እሴታችንን በተደራጀ መልኩ ለማሳየት ታሪካዊ ቦታችንን ለመጠበቅ፣ ለአገር ጎብኝዎችም በተደራጀ መልኩ ለማስተዋወቅ፣ ኢትዮጽያ በጎንደር ብሄራዊ የጎዳና ድግስ በተሰኘ የጥንታዊትዋ ኢትዮጽያ መዲና ጎንደር በያዝነዉ ሳምንት የጥምቀት በአል እድምተኞችን በማስተናገድ ላይ ትገኛለች። ኢትዮጽያ በጎንደር ብሄራዊዉ የጎዳና ድግስ ምን ይሆን ? የለቱ ዝግጅታችን የጎንደር ከተማ ከኒቲባ አቶ ሃብታሙ ገነቱን፣ የዝግጅቱን ዋና አስተባባሪ አቶ ሄኖክ ስዪምን፣ እንዲሁም በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቅርጽ እና ጥናት ጥበቃ ኤክስፐርትን አወያይቶ ይዞአል፣ ጥንቅሩን ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ
ሂሩት መለሰ