1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ብሪታኒያ የተገን ጠያቂዎች ቁጥር

ሐሙስ፣ ነሐሴ 26 2008

በብሪታኒያ የተገን ጠያቂዎች ቁጥር ከአስራ ሁለት አመት ወዲህ ከፍተኛ ጭማሪ አሳየ። የብሪታኒያ ፖለቲከኞች ከአውሮጳ ኅብረት ለመውጣት ያቀረቡት አንዱ ይኽው የተገን ጠያቂዎችን ቁጥር ለመቀነስ ነበር።

https://p.dw.com/p/1JuRe
Frankreich Flüchtlingslager Jungle in Calais
ምስል Getty Images/AFP/P. Huguen

[No title]

መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የብሪታኒያ መንግስትን በፍርድ ቤት ከሰው ካሸነፉ በኋላ በፈረንሳይ ካሊያስ ይገኙ የነበሩ ስደተኞች ወደ ብሪታኒያ ለመግባት ችለዋል። ከካሊያስ ወደ ብሪታኒያ በመጓዝ ቤተሰባቸውን ከተቀላቀሉ መካከል ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ይገኙበታል። ብሪታኒያ የተገን ጠያቂዎች ቁጥር ጨመረ ትበል እንጂ ከአውሮጳ አገራት እንኳ ሲነፃጸር ቁጥሩ አነስተኛ ነው ተብሏል።
ሐና ደምሴ
እሸቴ በቀለ