1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተቃዉሞ በባህርዳርና በፍኖተሰላም

Merga Yonas Bulaሐሙስ፣ ነሐሴ 19 2008

ባለፉት ሳምንታት በአማራ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ተቃዉሞ ተካሂዶዋል። ተቃዉሞዉ መንገድ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ መዉጣትን ጨምሮ የስራና የትራንስፖርት አድማ አካቶ እንደነበረ ዘገባዎች ያመለክታሉ።

https://p.dw.com/p/1Jpir
Karte Äthiopien Amhara, Tigray, Oromia Englisch

[No title]

ባሳለፍናቸው ቀናትም በባህርዳር፣ በፍኖተ ሰላም፣ በደብረማርቆስና በተለያዩ ቦታዎች የስራና የትራንስፖርት አድማ መደረጉ ተሰምቶ ነበር።


በአከባብዉ የሚኖሩ ነዋርዎች ያዩትንና የታዘቡትን እንዲያጋሩን ጠይቀን ነበር። የአማራ ክልል ርፅሰ መድና የሆነችሁ ነዋር የሆኑት ግን ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉ በመድናዋ የሰራና የትራንስፖርት አድማ በዋናነት እሁድ የተጀመረዉ ትላንት መጠናቀቁን ይናገራሉ። ዛሬ ከተማ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ተመልሳለች ይላሉ።

በዝህ ጉዳይ ላይ መንግስት ዝምታ መምረጡንና ከመህበረሰቡ አንድ አንድ ሰዎች ትራንስፖርት መቋረጡ መጀመርያ ላይ አስቆጥቷቸዉ እንደነበር እኝህ የባህርዳር ነዋር ይናገራሉ።

በምዕራብ ጎጃም ዞን የምተገኘዉ የፊኖተ ስለም ከተማ ነዋር የሆኑት ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የጠየቁት የአድማ መምታት ቅስቅሳዉ ከትላንት በስትያ በወረቀት ተበትኖ እንደበር ይናገራሉ።

በዛሬ እለት ተቃዉሞዉ መቀጠሉን ተናግሮ በከተማዋ የትራንስፖርት እንደሌሌ፣ ሱቆችና ሆቴሎች ዝግ መሆናቸዉን ይናገራሉ።

ሌላ ነዋርነታቸዉ በአድስ አበባ ያደረጉት የ ፊኖተሰላም ተዋለጅ የሆኑት ያለዉን ሁኔታ ቤቴሴቦቼ ጋር በስልክ ደዋዊያለዉ ይላሉ።

በክልሉ እየተደረገ ያለዉን ተቃዉሞ በተመለከተ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በክልላቸዉ እየተደረገ ያለዉ «ሁከትና ግጭት ከዚህ በላይ እንዲቀጥል መንግስት እንደማይፈቅድ» መሆኑ የአገር ዉስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ፕሬዝዳንቱ እንደ ምክንያትነት ሲጠቅሱ ተቃዉሞዉ «መላው ህብረተሰብ ጭንቀትና ፍርሀት» እያሳደረባቸዉ መሆኑን እና «ችግሩ ባለባቸው አካባቢዎች በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ችግር እየተከሰተ» መሆኑን ገልጠዋል።

መርጋ ዮናስ

አሪያም ተክሌ