1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተቃዉሞ በአዲስ አበባና አከባቢዋ

ረቡዕ፣ መስከረም 25 2009

በኦሮሚያ ልዩ ዞን አንዱ ከተማ የሆነችዉ በቡራዩ ከተማ የተካሄደዉ ተቃዉሞ እንደነበር በተለምዶዉ ዋላጋ ሰፈር ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/2Qu82
Addis Ababa (Äthiopien)
ምስል picture alliance/landov

Addis Shivers from the Protests in Oromia - MP3-Stereo

ከትላንት ጀምሮ በአዲስ አበባ አከባቢ በተለይም፤ ወደ ቡራዩ፤ ሰበታ፣ ጃሞ፣ በአዲስ ዓለምና ሌሎች አከባቢዎች ሁሉ ተቃዉሞ መታየቱንና በከተማይቱ ዉስጥ አንድ አንድ ቦታዎች የፀጥታ ስጋት መኖሩ ለመረዳት ተችሎአል። ይሁን እንጅ የመንግስት ባለስልጣናት ይህ ሁሉ «የፀረ ሰላም ኃይሎች ከሚያናፍሱት ወሬ» ነዉ ሲሉ ለጉዳዩ መልስ ሰጥተዋል።


አንድ ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የጠየቁን የአዲስ አበባ ነዋሪ ቢሾፍቱ ከአዲስ አበባ 40 ኪ,ሜ ባነሰ ርቀት ላይ የምትገኘዉ በመሆኗ አሁን በአድስ አበባና አከባብዉ የተፈጠሩት ዉጥረት ይጠበቅ ነበር ሲሉ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።


በአዲስ አበባ አከባቢ ያሉት ከተሞችም፣ እንድነ ቡራዩ፣ አየር ጤና፣ ጃሞና ሌሎች ቦታዎች ላይ ችግሮች እንደነበሩ ተናግረዉ በአዲስ አበባ ዉስጥ ያሉትንም ዉጥረቶች ያባባሰዉ ያ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል። በኦሮሚያ ልዩ ዞን አንዱ ከተማ የሆነችዉ በቡራዩ ከተማ የተካሄደዉ ተቃዉሞ እንደነበር በተለምዶዉ ዋላጋ ሰፈር ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።  

Äthiopien Anti-Regierungs-Protesten
ምስል REUTERS/T. Negeri


«እኔ ያየሁት በአከባቢዉ ላይ ትልቅ ርብሻ እንደነበረ ነዉ። መንገድ  ዘግተዉ መፈክራቸዉን ስያሰሙ ነበር። ግን የፀጥታ ኃይል አስለቃሽ ጢስና መሳርያን በመቶከስ ሰልፈኞቹን በትነዋል። ከእሁድ ከቀትር በኋላ ጀምሮ እስከ ዛሬ ሰዎች ሱቆቻቸዉን ሙሉ በሙሉ ዘግተዋል። የሻዬና ቡና ቤቶችም ሆነ ሆቴሎች ዝግ ናቸዉ። በሰበታ፣ በዓለምገና አሸዋ ሜዳ አከባቢዎች ደዉዬ ነበር። በእነዛም አካባቢዎች  ፋብሪካዎችና መኪናዎችን እንዳቀጠሉና እስካ ዛሬ መንገዶች መዘጋታቸዉን ነዉ የሰማሁት።»


የፀጥታ ኃይሉ በወሰደዉ ርምጃ የተጎዱ ሰዎች መኖር አለመኖራቸዉ  ርግጠኛ ባይሆኑም፣ አንድ የከታ ነዋሪ፣ በርካታ ወጣቶች በመኪና ተጭነዉ መወሰዳቸዉንና በየቤቱ እየሄዱ ወጣቶችን ከቤት ስያወጡ አይቻለዉ ብለዋል። ሰዎች ለአራት፣ ለአምስት መንገድ ላይ ተሰብስበዉ ከቆሙም አስፈራርተዉ እንደሚበትኗቸዉም ጠቅሰዋል። 


በመንግስት በኩል ጉዳዩን በተመለከተ የተቀናጀ መረጃ ለማገኘት ስንል ያደረግነዉ ሙከራ አልተሳካም። ይሁን እንጅ የሃገር ዉስጥ መገናኛ ብዙኃን የአገርቱን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኃላፊ ጄኔራል አሰፋ አብዩ ጠቅሶ እንደዘገበዉ “በአዲስ አበባ ፀረ ሰላም ሀይሎች ከሚያናፍሱት ወሬ ውጪ ከተማዋ በሰላማዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ትገኛለች” ሲሉ መናገራቸዉን ዘግበዋል።ስለ አዲስ አበባ የዛሬ ውሎ የአዲስ አበባውን ዘጋቢያችንን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔርን በስልክ አነጋግረናል ።

መርጋ ዮናስ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ