1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተቃዋሚ የኦሮሞ ፓርቲዎች ጥያቄ

ሐሙስ፣ መጋቢት 14 2009

የኦሮሞ ሕዝብ ከአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም እንደሚያገኝ በሕገ-መንግስት ቢጠቀስም እስካሁን ገቢር አልሆነም

https://p.dw.com/p/2Zpzn
Addis Ababa (Äthiopien)
ምስል picture alliance/landov

(Beri.AA) Oromo opposition parties - MP3-Stereo

የኦሮሞ ሕዝብ ከአዲስ አበባ መስተዳድር ማግኘት የሚገባዉን ልዩ ጥቅም እስካሁን እስካሁን አለማግኘቱ ቅር እንዳሰኛቸዉ አራት ተቃዋሚ የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስታወቁ።የኦሮሞ አቦ ነፃነት ግንባር፤ የኦሮሞ ነፃነት አንድነት ግንባር፤የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ እና የኦሮሚያ ነፃነት ብሔራዊ ፓርቲ በጋራ እንደሚሉት የኦሮሞ ሕዝብ ከአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም እንደሚያገኝ በሕገ-መንግስት ቢጠቀስም እስካሁን ገቢር አልሆነም።የፓርቲዎቹ ተወካዮች አዲስ አበባ ሲሆን ሙሉ በሙሉ በኦሮሚያ መስተዳድር ሥር እንድትሆን ይሕ ቢቀር የጥምር አስተዳደር እንዲመሰረትላት ጠይቀዋል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን  የሁለቱን ፓርቲዎች ተወካዮች አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለማርያም

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ