1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተቃውሞ በለንደን የኤርትራ ኤምባሲ

ዓርብ፣ ጥር 17 2005

ተቃዋሚዎቹ እርምጃውን የወሰዱት ኤምባሲው እንደማይፈራ ህዝቡ እንዲያውቅ ለማድረግ፤ እንዲሁም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱና የመንግሥትም ሥልጣን ለህዝብ እንዲሰጥ ለመጠየቅ መሆኑን ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/17RnH
21.01.2013 Karte Eritrea Asmara eng

ወደ 20 የሚሆኑ ከኤርትራ ማህበረሰብና ድርጅቶች የተውጣጡ የኤርትራ መንግስት ተቃዋሚዎች ሎንዶን የሚገኘዉን የኤርትራ ኤምባሲ በትናንትናው እለት ጥሰው ገቡ። ተቃዋሚዎቹ እርምጃውን የወሰዱት ኤምባሲው እንደማይፈራ ህዝቡ እንዲያውቅ ለማድረግ፤ እንዲሁም  የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱና የመንግሥትም ሥልጣን ለህዝብ እንዲሰጥ ለመጠየቅ መሆኑን ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ኤምባሲው ውስጥ የተሰቀለውን የኤርትራውን ፕሬዝዳንት የኢሳያስ አፈውርቂን ፎቶግራፍ አውርደው የጣሉት ተቃዋሚዎች አምባሳደሩን ለማነጋገር እንዳልቻሉም አስታውቀዋል። ዶቼ ቬለ ስለተቃውሞው በለንደን የኤርትራ ኤምባሲን አስተያየት ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። ወኪላችን ድልነሳው ጌታነህ ዝርዝር ዘገባ አለው ።
 

ድልነሳው ጌታነህ

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ