1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተጨማሪ የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎች ታሰሩ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 4 2009

የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈዉ መስከረም ማብቂያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ ወዲሕ ብቻ ከአንድ መቶ ሐምሳ በላይ የፓርቲዉ መሪዎችና አባላት ታስረዋል

https://p.dw.com/p/2UCsl
ምስል DW

(Beri.AA) Äth.Blau Partei-Verhaftung - MP3-Stereo

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ማሕበር ሰማያዊ ፓርቲ የመንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች በአባላቱና በመሪዎቹ ላይ የሚያደርሱባቸዉ ወከባ እና እስራት መቀጠሉን አስታወቀ።የፓርቲዉ ፕሬዝደንት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት እንዳስታወቁት ሰሞኑን በባሕር ዳር እና በሐይቅ ከተሞች ሰባት የፓርቲዉ መሪዎች ታስረዋል።የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈዉ መስከረም ማብቂያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ ወዲሕ ብቻ ከአንድ መቶ ሐምሳ በላይ የፓርቲዉ መሪዎችና አባላት ታስረዋል።በፕሬዝደንቱ መግለጫ መሠረት እስረኞቹን የፓርቲዉ መሪዎች፤ ቤተሰቦችም ሆኑ ጠበቆች ማነጋገር አልቻሉም።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ