1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቱርክ እና የአሜሪካን የኒዩክልየር ጦር መሣሪያዎች

ሰኞ፣ ነሐሴ 16 2008

አሜሪካን ቱርክ የሚገኙት የጦር መሣሪያዎቿ ባልታወቁ ወገኖች እጅ እንዳይገባ መሣሪያዎቹን ከቱርክ እናውጣ የሚለው ሃሳብ አሁን እየተጠናከረ መጥቷል ።

https://p.dw.com/p/1JnB0
Türkei1.JPG

[No title]

የቱርክ እና የአውሮፓ ህብረት እንዲሁም የቱርክ እና የዩናይትድ ስቴትስ ግንኙነት እየሻከረ ሄዷል ። በተለይ ከመንግሥት ግልበጣ ሙከራው በኋላ የአንካራ መንግሥት የዩናይትድ ስቴትስ እጅ አለበት ብሎ መክሰሱ ውዝግቡን አባብሶታል ። በቱርክ እና በቱርክ አጎራባች አገሮች የሚታየው እንቅስቃሴ እን የቦምብ ጥቃቶችም እንዲሁም ራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራው ቡድን ሽብር ፈጠራም የአሜሪካንን መንግሥት እያሳሰበው መጥቷል ። አሜሪካን ቱርክ የሚገኙት የጦር መሣሪያዎቿ ባልታወቁ ወገኖች እጅ እንዳይገባ ከቱርክ እናውጣ የሚለው ሃሳብ አሁን እየተጠናከረ መጥቷል ። በዚህ ላይ አትኩሮ የተካሄደ የአንድ ጥናት ውጤትን ያካተተ ዘገባ በቅርቡ ይፋ ተደርጓል ።የዶቼቬለው አንድርያስ ቤከር ያጠናቀረውን የዘገባውን ፍሬሃሳቦች ይልማ ኃይለ ሚካኤል እንደሚከተለው አሰባስቦታል ።

አንድርያስ ቤከር /ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ