1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቱርክና የኤርዶጋን ቀጣይ የአመራር ዘይቤ፣

ሰኞ፣ ነሐሴ 5 2006

እ ጎ አ፣ ከ 2003 ዓ ም አንስቶ ፣ ላለፉት 11 ዓመታት ገደማ ፣ ቱርክን በ ጠ/ሚንስትርነት ሲያስተዳድሩ የቆዩት ሪቸፕ ጣይብ ኤርዶጋን፣ በዚያች ሀገር ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሬዚዳንት በህዝብ እንዲመረጥ በተደረገበት ደንብ፤

https://p.dw.com/p/1CsYa
ምስል picture alliance/AA

ትናንት ፣ ሦስት ተወዳዳሪዎችን ለመምረጥ አደባባይ ከወጣው ህዝብ መካከል የ 51,74 ከመቶውን የድምፅ ድጋፍ በማግኘት አሸናፊ ለመሆን በቅተዋል። በቱርክ የሚኖሩ የአገሪቱ ዜጎች ብቻ ሳይሆኑ በውጭ ሃገራት የሚኖሩት የአገሪቱ ተወላጆችም ለመጀመሪያ ጊዜ ባሉበት ድምፅ እንዲሰጡ ስለተፈቀደላቸው፤ በጀርመን ሀገር ከሚኖሩት ---ሚሊዮን ቱርኮች መካከል ድምፅ ለመስጠት ብቁ የሆኑት 1,4 ሚሊዮኑ በዚሁ አዲስ ደንብ ተጠቅመዋል።

ቱርክን ለማዘመን ጥረት እንዳደረጉና በኤኮኖሚው መስክ እንደተሳካላቸው የሚነገርላቸው ኤርዶጋን፤ የአምባገነንነት ባሕርይ ይንጸባረቅባቸዋል የሚል ትችት ሲሰነዘርባቸው መቆየቱ አይዘነጋም። ትናንት በምርጫ ካሸነፉ በኋላ እኩለ ሌሊት ገደማ ላይ ባሰሙት ንግግር በፓርቲዎፖች መርኀ ግብር ሳቢያ ፣በአቋም የተከፋፈለው ሕዝብ እንዲቀራረብ ለዘብ ያለ ዕርቅ አዘል ንግግር ማሰማታቸው ነው የተገለጠው።

ገበያው ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ