1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ታሪካዊው የአየር ንብረት ለዉጥ ስምምነት

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 4 2008

የዓለም የሙቀት መጠን ጭማሪን ከ2.0 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ለማቆየት ቅዳሜ ዕለት ፓሪስ ላይ የተፈረመው ስምምነት ትልቅ ስኬት እንደሆነ ተነግሮለታል።

https://p.dw.com/p/1HNCi
Frankreich Cop21 Klimagipfel in Paris Demonstration
ምስል picture-alliance/AP Photo/Greenpeace

195 ሀገራት ያጸደቁትን ይህንኑ የፓሪስ ስምምነት የጀርመኗ መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት ቁርጠኝነቱን ያሳየበት ነበር» ብለውታል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ባን ኪ ሙን እንዲሁም የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርሲያን ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሳይቀሩ ስምምነቱን አወድሰዋል። ጉባዔው እንደ ቻይና እና ሌሎች በርካታ ሀገራት በመሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ባለመግባባታቸው ለአንድ ቀን መገፋቱ ይታወሳል። አሁን ሀገራቱን መልሶ ስላስማማው ስለዚሁ የጉባዔ ውጤት እና ቀጣይ ርምጃ ብራስልስ የሚገኘው ወኪላችን ገበያው ንጉሴን ጠይቀንዋል።

ገበያው ንጉሴ

ልደት አበበ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ