1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ታዳሽ የኃይል ምንጭ

ዓርብ፣ ሰኔ 20 2000

ኢትዮጵያ ከተክል ለሚገኘዉ ታዳሽ ኃይል ማልትም ባዮ ፊዩል ትኩረት ሰጥታለች፤ በየዓመቱም ከሸንኮራ ብቻ አንድ ቢሊዮን ሊትር ኤታኖል ለማምረት ታልሟል።

https://p.dw.com/p/EQps
ለተፈጥሮ ነዳጁ የሚዉል ተክልምስል AP

ለታዳሽ የኃይል ምንጭነት ከሸነኮራ አገዳ በተጨማሪ የማሽላና የበቆሎ አገዳዎች፤ እንዲሁም የጉሎ ዛፍ፤ ጃትሮፋ የተባለዉ ተክልና የዘንባባ ዛፍም ይዉላሉ። ከእነሱ የሚገኘዉም ፍሳሽ መሆኑን ባለሙያዉ አቶ መልስ ተካ አስረድተዋል። ኢትዮጵያ በዋናነት ይህን የታዳሽ ኃይል ለመጠቀም ያለመችዉ አንድም ለነዳጅ የሚወጣዉን የዉጭ ምንዛሪ ለመቆጠብ፤ አማራጭ የኃይል ምንጭ ለማጠናከርና ብክለትንም ለመከላከል ነዉ።