1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትምህርትን ማዳረስ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 13 2009

ኢንተርኔትን በሚገድቡ እንደ ኢትዮጲያ ባሉ ሀገራት ደግሞ የሳተላይት ቴክኖሎጂ ትምህርትን ለማዳረስ አማራጭ መንገድ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።

https://p.dw.com/p/2UjPH
Schüler in einem Dorf in Äthiopien
ምስል picture-alliance/ dpa

Beri Wash.(Promoting educatilon in Africa using modern technology) - MP3-Stereo

የተመ የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ድርጅት በምህጻሩ የዩኔስኮ ዘገባ እና ሌሎችም ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሰሀራ በስተደቡብ ባሉ የአፍሪቃ ሀገራት ወደ ትምህርት ቤት የሚሄዱ ህጻናት ቁጥር ዝቅተኛ ነው  ። ትምህርት ከሚጀምሩት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የአካባቢው ሀገራት ህጻናት በመምህራን እና በትምህርት መሣሪያዎች እጦት በርካቶች የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸው መጨረስ አይችሉም ።  አንድ መምህር እና የህክምና ባለሞያ ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት በነዚህ አካባቢዎች ኢንተርኔት ብቻ በመጠቀም ትምህርትን በስፋት ማዳረስ እንደሚቻል ተናግረዋል ። ኢንተርኔትን በሚገድቡ እንደ ኢትዮጲያ ባሉ ሀገራት ደግሞ የሳተላይት ቴክኖሎጂ ትምህርትን ለማዳረስ አማራጭ መንገድ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችል እኚሁ ምሁር አስረድተዋል። የዋሽንግተኑ ወኪላችን ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።

 
መክብብ ሸዋ 


ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ