1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትምባሆን የሚመለከተው አዲስ ህግ

Lidet Abebeዓርብ፣ የካቲት 25 2008

ከመጋቢት ወር አንስቶ ኢትዮጵያ ውስጥ ህዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ትምባሆ ማጨስ በህግ የተከለከለ ይሆናል። ትምባሆን የሚመለከተው አዲስ ህግ ኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ ሊሆን ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል።

https://p.dw.com/p/1I6bX
Rauchverbot in Äthiopien
ምስል James Jeffrey

ትምባሆን የሚመለከተው አዲስ ህግ

ስለዚሁ ህግ ምንነት በኢትዮጵያ፣ ምግብ መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን የህግ ዝግጅት ክፍል ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ አብረኸት ግደይ ገልጸውልናል።

ህዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ትምባሆ ሲያጨስ የተገኘ ሰውን ወይም እንዲጨስ የፈቀደ ተቋም ህጉን ሳያከብር ቢቀር ቁጣቱ ምንድን ነው? የህግ ባለሙያዋ ወ/ሮ አብረኸት ፤ ይህ እንደየ ክልሉ እና የማስፈፀሚያ ህኑ ይለያያል ይላሉ። ህዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ትምባሆ ማጨስን ወይም እንደ አንድ ተቋም ሌሎች እንዲያጨሱ መፍቀድን ስለሚከለክለው ህግ ይህን ያህል ከሰማን፤ ተግባራዊ ማድረግ የሚጠበቅበት ማህበረሰብስ በዚህ ላይ ምን አስተያየት አለው? የጥቂት ወጣቶችን አስተያየት አሰባስበናል።
ሙሉውን ዝግጅት በድምፅ ያገኙታል።


ልደት አበበ
አርያም ተክሌ