1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ነታንያሁ በዋይት ሃስው ያልተፈለጉ እንግዳ

ማክሰኞ፣ የካቲት 24 2007

ቦነር ነታንያሁን የጋበዙት እኛን ሳያማክሩ ነው ከሚሉት የዴሞክራት ፓርቲ እንደራሴዎች ወደ 40 ያህሉ ንግግሩን ላይ እንደማይገኙ አስታውቀዋል ።

https://p.dw.com/p/1EkLg
USA Washington AIPAC Konferenz Benjamin Netanjahu Ministerpräsident Israel
ምስል REUTERS/Jonathan Ernst

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ነታንያሁ ዛሬ ለአሜሪካን ምክር ቤት ያደርጋሉ የተባለው ንግግር ማወዛገቡ ቀጥሏል ።ነታንያሁ በአሜሪካን ምክር ቤት አብላጫ ድምፅ ባላቸው በሪፐብሊካኖች አፈ ጉባኤ ጆን ቦነር ለምክር ቤቱ ንግግር እንዲያደርጉ መጋበዛቸው ዴሞክራቶችን አስቆጥቷል ። ቦነር ነታንያሁን የጋበዙት እኛን ሳያማክሩ ነው ከሚሉት የዴሞክራት ፓርቲ እንደራሴዎች ከ60 በላይ የሚሆኑት ንግግሩን ላይ እንደማይገኙ አስታውቀዋል ። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራካ ኦባማ ዋሽንግተን ቢሆኑም የእስራኤል ምርጫ በተቃረበበት በዚህ ወቅት ነታንያሁን የማነጋገር እቅድ እንደሌላቸው ተናግረዋል ። ነታንያሁ ዛሬ ለአሜሪካን ምክር ቤት የሚያሰሙት ንግግር በኢራን የኑክሌር መረሐ-ግብር ላይ እንደሚያተኩሩ አስታውቀዋል ። ነታንያሁ ትናንት ለአንድ አይሁድ ድርጅት እንደተናገሩት አሜሪካንና እስራኤል ኢራን የኒዩክልየር ጦር መሣሪያ ባለቤት እንዳትሆን የሚስማሙ ቢሆንም በአፈፃፀሙ ላይ ግን ልዩነት አላቸው ።መክብበ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝሩን ልኮልናል

መክብብ ሸዋ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ