1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ኑስኪ ትያትር እንይ» የትያትር ፊስቲቫል አዲስ አበባ

ሐሙስ፣ ኅዳር 11 2007

የሰዉ ልጅ በሚያደርገዉ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ዉስጥ ጥበብ እንዳለ ባለሞያዎች ይናገራሉ። የሰዉ ልጅ ይህን እንቅስቃሴዉን በማስመሰል በትያትር መልክ ለራሱ ተዉኖ ያቀርበዋል፤ እንደ መስታወትም ገሃዱን ዓለም ራሱን ያይበታል፤ በትያትር። ትያትር እንደሚታሰበዉ ለሳቅ ለጫወታ ለመዝናኛ የሚቀርብ ሳይሆን፤ ትያትር «የሃገር የህዝብ ፍልስፍና ፤

https://p.dw.com/p/1DqdS
Äthiopien Nationaltheater in Addis Abeba
ምስል DW

ቋንቋችንን፤ ባህላችንን ማንነታችንን የምናይበት ሰፊ የጥበብ ገበታ መሆኑን የጥበቡ ባለሞያዎች ይናገራሉ። አንድ መቶ ዓመት እንዳስቆጠረ የሚነገርለት የሃገራችን የዘመናዊ የትያትር ጥበብ ፤ በዘርፉ ዘንድ አሻራቸዉን ያሳረፉ በርካታ ዘመናዊ ጠቢባን ለዘርፉ ማበብ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ እጅግ መድከማቸዉ ተመልክቶአል። በሃገራችን የዘመናዊ ትያትር ጥበብ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ባለፈዉ ሰሞን የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የትያትር ጥበባት ት/ቤት ለሳምንት የዘለቀ የትያትር ፊስቲቫል አድርጎ በጥበቡን ባለታሪኮች በማወደስ በጥበብ ሥራቸዉ ዙርያ ተወያይቶአል። በትያትር ጥበባት ት/ቤት የሚሰሩት ትያትሮች ተመልካች ጋር አይደርሱም፤ ህዝብ ሳያጣጥማቸዉ መክነዉም እየቀሩ ነዉ የሚል አስተያየት በብዛት በመምጣቱ ትምህርት ቤቱ በሰፊዉ የትያትር ፊስቲቫልን ለማዘጋጀት መነሳሳቱን በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የትያትር ጥበባት ትምርት ክፍል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ እሸቱ ገልፀዉልናል። «ኑስኪ ትያትር እንይ» በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ለሳምንት የዘለቀዉ የትያትር ፊስቲቫል ደማቅ እንደነበርም ተነግሮለታል። በ 20ኛዉ ክፍለ ዘመን መጀመርያ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደስላሴ በማጂስቲ ሆቴል ወይም ራስ ትያትር ንጉሱን መኳንቱን እና ለሹማምንቱን በአዲስ አበባ ወጣቶች የቀረበዉን ሙዚቃዊ ተዉኔት ካሳዩ በኋላ ይህን ትያትር የተከታተሉት እና በዝያን ግዜ ራሽያ ትምህርትን ተምረዉ የተመለሱት በጅሮንድ ተክለሃዋርያት ተክለማርያም ለካ የሃገሪ ሰዉ ትያትርን አያዉቅምና ፋቡላ ብዬ የጻፍኩትን የግጥም መድብሌን የአዉሪዎች ኮሞዲያ ብዬ ለትያትር አቀረብኩት ብለዉ መናገራቸዉ ተጠቅሶአል። በየዛሬ 100 ዓመት ግድም በበጅሮንድ ተክለሃዋርያት ተክለማርያም በፅሑፍ የቀረበዉ ትያትር፤ የመጀመርያዉ የኢትዮጵያ የዘመናዊ ትያትር መሆኑን የዘርፉ ባለሞያዎች ይናገራሉ። በጅሮንድ ተክለሃዋርያት ተክለማርያም ከተደረሰዉ ትያትር ጀምሮ የኢትዮጵያ ትያትር ቅኝት ምን ይመስል ይሆን? ቆየት ብሎ በ1970ዎቹ መጀመርያ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የትያትር ጥበብ ክፍል መመስረቱም ይታወቃል። ተቋሙ ባለፈዉ ሰሞን ለኢትዮጵያ ትያትር ጥበብ እድገት አስተዋፅኦ ያደረጉ ባለሞያዎችን በማወደስ ስራቸዉ ለዉይይት አቅርቦአል። በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የትያትር ጥበባት ትምርት ክፍል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ እሸቱ ያዘጋጀነዉ ፊስቲቫል ልዩ ልዩ ዘርፎችን በተመለከተ ነበር ሲሉ አብራርተዉልናል። በዓለማቀፍ የክዋኔ ጥበብ ምርምር ዘርፍ የከፍተኛ ትምህርታቸዉን በእንግሊዝ፤ ሆላንድ እና ሰርብያ ያጠናቀቁት የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የትያትር ጥበባት ትምርት ክፍል መምህር አቶ ዘሪሁን ብርሃኑ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴን በትያትር ጥበብ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ በተደረገዉ ፊስቲቫል ላይ አቅርበዋል። ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።


አዜብ ታደሰ
ተክሌ የኋላ