1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኔቶ ቱርክ እና የፓትሪየት ሚሳይል

ማክሰኞ፣ ኅዳር 25 2005

28 የሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ኪዳን፡ ኔቶ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች የኪዳኑ አባል የሆነችው ቱርክ ከሶርያ ሊሰነዘር የሚችልን ጥቃት የሚችልን ጥቃት ለመከላከል ትችል ዘንድ ፣ ኔቶ ቱርክ ወሰኗ ላይ ልትተክለው

https://p.dw.com/p/16vl7
KOERBECKE, GERMANY - MAY 19, 1999: (FILE PHOTO) German soldiers tend to a Patriot anti-missle system May 19, 1999 in Koerbecke, Germany. The German military will loan two batteries of its Patriot systems to Israel, including 128 missiles, at the end of January 2003 to help Israel defend itself against possible Iraqi Scud missile attacks should a war against Iraq break out. (Photo by Deutsche Bundeswehr/Getty Images)
ፀረ ሚሳይሉ ሮኬት «ፓትሪየት»ምስል Getty Images

የምትችል «ፓትሪየት» የተባለውን ፀረ ሚሳይሉን ሮኬት እንዲያቀርብላት ከሁለት ሣምንት በፊት ባቀረበችው ጥያቄ ላይ ዛሬ መከሩ። ከምክክሩ በኋላ ኪዳኑ ፓትሪየት ፀረ ሚሳይሉ ሮኬት በቱርክ እንዲተከል ወስኖዋል።  እስካሁን የዚሁ እጅግ ዘመናይ የሆነው የ«ፓትሪየት» መሣሪያ ባለቤት የሆኑት ሦስት ሀገራት ጀርመን፡ ኔዘርላንድስ እና ዩኤስ አሜሪካ ብቻ ሲሆኑ፣ ጀርመን ይህንኑ የጦር መሣሪያ ለቱርክ ለመስጠት ዝግጁ መሆንዋን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጊዶ ቬስተርቬለ ቀደም ሲል ገልጸዋል። ፀረ ሚሳይሉ ሮኬት ለቱርክ ከመስጠቱ ጥያቄ ጋ በተያያዘው የጀርመን ወታደሮች ሥምሪት ላይ የጀርመን ፌዴራዊ ምክር ቤት በዚህ ወር ውሳኔ ማሳለፍ ይኖርበታል። ቱርክ በጎረቤት ሶርያ የቀጠለው የርስበርስ ጦርነት ለሀገርዋ ፀጥታ ስጋት እንደደቀነ ተሰምቶታል።  ስለ ሚሳኤል ተከላው አስፈላጊነት እንዲሁም   የሶሪያውን የርስ በርስ ጦርነት ለማቆም በሚደረገው ጥረት ላይ ሊሳድር ስለሚችለው ተፅእኖና ስለሩስያ አቋም የብራሰልሱን ወኪላችንን ገበያው ንጉሴ በስልክ አነጋግሬዋለሁ። 

NATO Secretary-General Anders Fogh Rasmussen holds a news conference ahead a two-day NATO foreign ministers at the Alliance's headquarters in Brussels December 4, 2012. NATO foreign ministers will agree on Tuesday to send Patriot missiles to beef up Turkey's air defenses and calm Turkey's fears that it could come under missile attack, possibly with chemical weapons, from Syria, diplomats said. REUTERS/Yves Herman (BELGIUM - Tags: MILITARY POLITICS)
የኔቶ ዋና ፀሐፊ አንደርስ ፎኽ ራስሙሰንምስል Reuters

ገበያው ንጉሴ

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ      

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ