1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አልበሽር በአስመራ

ሰኞ፣ መጋቢት 14 2001

የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ ከቆረጥባቸው ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሱዳን ውጭ ኤርትራን ለመጎብኘት ዛሬ ረፋድ ላይ አስመራ ገብተዋል ።

https://p.dw.com/p/HIBS
ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽርምስል AP

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው አልበሽር አሰመራ የገቡት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ባደረጉላቸው ግብዣ መሰረት ሲሆን ኤርትራ የሚቆዩትም ለአንድ ቀን ነው ። የኤርትራው ፕሬዝዳንት አጋርነታቸው በመግለፅ የሱዳኑ መሪ ኤርትራን እንዲጎበኙ የጋበዙዋቸው ዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት በአልበሽር ላይ የዕስር ማዘዣ በቆረጠ በሳምንቱ ነበር ። አልበሽር አስመራ የገቡት በአረብሊግ ስብሰባ ላይ ለመካፈል ወደ ዶሀ እንዳይሄዱ የሀገሪቱ ከፍተኛ የሀይማኖት መሪዎች በጠየቁ ማግስቱ መሆኑ ነው ። የአስመራው ወኪላች ጎይቶም ቢሆን ዘገባ አለው