1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአረና ሊቀመንበር ተደበደቡ፤፤

ሰኞ፣ ሰኔ 5 2009

የአረና ትግራይ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አብርሃ ደስታ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በመቀሌ ከተማ ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል፡፡ ወጣቱ ፖለቲከኛ ባለፈው ቅዳሜ ከምሽቱ አንድ ሰዓት አካባቢ ወደ ቤቱ በመሄድ ላይ እየሄደ እያለ ነው ድብደባ ያጋጠመው፡፡

https://p.dw.com/p/2eYPN
Äthiopien Abreha Desta in Mekelle
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

Ber. Addis Ababa (Unidentified people attack Arena Party Chief) - MP3-Stereo

 የአረና ትግራይ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አምዶም ገብረስላሴ ጥቃቱ “የግድያ ሙከራ ይመስላል” ሲሉ ለዶይቸ ቬለ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በፓርቲው አባላት ላይ የደረሱ ድብደባዎችንና ግድያዎችን በማስታወስም በአብርሃ ላይ የደረሰው ጥቃትም “ፖለቲካዊ ይዘት አለው” ብለዋል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚያብሔር አጠር ያለ ዘገባ አድርሶናል፡፡ 

ዮሐንስ ገብረ እግዚያብሔር

ተስፋለም ወልደየስ

አዜብ ታደሰ