1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አርአያ ያለዉ ምግባር ለፈፀሙ የዶይቼ-ቬለ ማበረታቻ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 23 2007

በማኅበረሰባችሁ ለየት ያለ ምግባር የሚያከናዉኑ ሰዎችን ታሪክ ያካፍሉን ግለሰቦቹ ስማርት ፎንና ሌሎች ሽልማቶችን ያገኛሉ።

https://p.dw.com/p/1FmyS
Local Heroes Artikelmotiv Amharisch PNG
ምስል DW

ዶይቼ-ቬለ በዓለም ላይ ለየት ያለ ነገር የሚያከናዉኑ ግለሰቦችን ማስተዋወቅ አለበት። ይኽ ማለት ዓለም አቀፍ ለዉጥ ለማምጣት የሚጥሩ፤ የሚያስቡና አዳዲስ ነገር ፈጣሪዎችን ማለት ነዉ። ደንቦችን ከማፍረስና ከማዛባት ይልቅ ለደንቦች የሚገዙ፤ የሰዎችን እንቅስቃሴ ከመገደብ ይልቅ የሚያነቃቁ ወገኖችን እንደግፋለን። እነዚህን ወገኖች መረጃ እንዲያገኙና ዓለምን እንዲለዉጡ ልንረዳቸዉ ይገባል።– በጀርመን የተሠራ፤ ለአዕምሮ የተሠራ (made in Germany, made for minds)

አርአያዊ ምግባርን ያከናወኑ ሰዎችን ዶይቼ-ቬለ የሚመጥንበት መመዘኛ
- ኦባማ የጋበዟቸው 13 ኢትዮጵያውያን ወጣቶች
- ዘረኝነት በምሥራቅ ጀርመን
ስለሌሎች አርአያዊ ምግባር ፈፃሚዎችና ስለዶይቼ-ቬለ እንግሊዘኛ ዜና የበለጠ መረጃ ለማግኘት dw.com/localheroes ይመልከቱ።

ጊዜ አያጥፉ ---- በአካባቢዎ አርአያነትን ስለፈፀሙ ሰዎች ታሪክ አሁኑኑ ይንገሩን።

በማኅበረሰባችን ዉስጥ ለየት ያለ ምግባር ስለአከናወኑ ሰዎች ማወቅ ወይም መስማት እንፈልጋለን። እነዚህ ሰዎች የተሻለ የሕክምና ዘዴና መድሐኒት ለማግኘት የሚጥሩ ናቸዉ? ወይስ ሥራ የሚያስገኝ ፋብሪካ የመሰረቱ? ግለሰቡ(ዋ) እርሶን ወይም አንተን ትምህርት ቤት ያደረሱ አያት ናቸዉ? በየመስኩ በተለያየ ደረጃ አካባቢያቸዉን ለማሻሻል የሚጥሩ ሰዎች አሉ። የእነዚህ ሰዎች ታሪክ መስማትና ማንነታቸዉን ለዓለም ማሳወቅ እንፈልጋለን። የሚከተለዉን ፎርም (እባክዎ በዚህ የኢሜል አድራሻ ይጻፉልን amharic@dw.com) ሞልተዉ ይላኩልን። በፌስ ቡክ በምናደርገዉ ዉይይት Facebook አማካኝነት ታሪኮን ያካፍሉን። አሸናፊዎቹ በተገቢዉ መንገድ ከቀረበልን መዘርዝር መካከል ይመረጣሉ። ተሳታፊዎች ለመሸለም ሕጋዊ ጥያቄ ማንሳት አይችሉም። ማመልከቻዎች በሙሉ እስከ ሐምሌ 12, 2007 ዓ.ም. መድረስ አለባቸዉ።


ሽልማቶች
- አንደኛ አሸናፊ፤ ስማርት ፎን እና የአርአያዊ ምግባር ሽልማት ጥቅል
- ሁለተኝና ሦስተኛ ደረጃ፤ አይፖድ እና የአርአያዊ ምግባር ሽልማት ጥቅል
- የተሳታፊ ማስተዛዘኛ ሽልማት፤ ከሰባቱ የአርአያዊ ምግባር ሽልማት ጥቅል አንዱን ያገኛሉ።