1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አስናቀች ወርቁ የመድረኳ ዕንቁ

ሐሙስ፣ መስከረም 11 2004

አስናቀች ተዋናይ የባህል ሙዚቀኛ፣ ክራር ተጫዋች፣ ድምጻዊት፣ የባህል ተወዛዋዥ፣ ዘመናዊ ዳንሰኛ፣ ገጣሚ ሁለገብ የጥበብ እመቤት ነበረች፣ ላትመለስ መስከረም አራት ሁለት ሽ አራት አመተ ምህረት ከዚህ አለም በሞት ተለይታናለች።

https://p.dw.com/p/Rn9D
አስናቀች ወርቁምስል DW

ዛሪ አስናቀች ወርቁን በስጋ የምንሰናበትበት ቀን ነዉ። ቀኑ መድረክ የሚያነባበት፣ ክራር በሃዘን የሚያንጎራጉርበት ነዉ!

በጀርመናዊዉ ፒት ቡደ በአስናቀች የክራር ድርደራ ተመስጠዉ፣ ዜማዋን አፍቅረዉ የአስናቀችን ሙዚቃ በዘመናዊዉ ሲዲ ለመጀመርያ ግዜ አካታዉ ወደ አለም የሙዚቃ መድረክ ይዘዋት ብቅ ያሉ ናቸዉ። በፈጣኑ የመገናኛ መረብ ኢንተርኔትም የህይወት ታሪኳን ከነሙዚቃዋ አሰራጭተዉላታልም። ጀርመናዊዉ የኪነ ጥበብ ሰዉ እንዳሉት የመድረኳ እንቁ ሞት የባህላዊዉን የክራር አጨዋወት ለዛ አብሮ እንዳይከስም፣ በተወችልን የጥበብ ማህደር ተምረን፣ አልባሳትዋን እና ክራርዋን የተቀረጸቻቸዉን የምስል ቅንብሮች፣ ለትዉልድ መሸጋገርያ ድልድይ፣ በቅርጽነት ለመታሰብያ፣ በክራር ድርደራ የጣት አጣጣል መማርያ፣ ካስቀመጥነዉ የጥበቧ እመቤት አስናቀች ወርቁን እያስታወስን ሌላ አንድ ሽህ አስናቀችን የምናገኝ ይመስለናል። በእለቱ ቅንብራችን የዛሪ አራት አመት አስናቀች ወርቁን ቤትዋ ድረስ በመሄድ ጎብኝተን ያነሳናት ፎቶ እና ለራድዮ ጣብያችን እቤትዋ አልጋ ላይ ሆና የሰጠችን ቃለ ምልልስ ይደመጣል። አስናቀች ፍቅርን በማፍቀርዋ ፍቅር ትዝታን ማዜም ብቻ ሳይሆን ስለ ፍቅር በመግጠሟ መፈቀር ማፍቀርዋን ብቻ ሳይሆን በግጥም ረገድ የስነ ግጥም ችሎታዋንም አስመስክራለች። ሙዚቃን ከተዉኔት ጋር እያጣመረች ክራርዋን በፍቅር እየገረፈች ስለፍቅር አዚማ በስጋ የተለየችን አስናቁ ስራዋ ህያዉ ሆና ለዘላለም ይኖራል። በስጋ የተለየቻቸዉ ቤተ ዘመዶችዋ የስራ አጋሮችዋ ወገኖችዋ ግባዕተ መሪቷ ሲፈጸም «ዛሪ አስናቀች ወርቁን በስጋ የምንሰናበትበት ቀን ነዉ። ይህ ቀን መድረክ የሚያነባበት፣ ክራር በሃዘን የሚያንጎራጉርበት ቀን ነዉ» ሲሉ ጽፈዉላታል። አዎ አስናቀች ወርቁ ድቅ ክራር ገራፊ፥ ልዩ ትዝታ ተጫዋች፥ ጎበዝ ተዋኝ ብቻ አልነበረችም። በተለያዪ አለም አገሮች ክሯርዋን ይዛ የኢትዮጽያን ባህላዊ ሙዚቃ መሳርያ ያስተዋወቀች፣ የአገርዋ አንባሳደርም ነበረች። ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!

Äthiopien Musiker Asnakech Worku Alemu Aga und Pit Budde
አስናቀች ወርቁ፣ፒት ቡደ፣ አለሙ አጋምስል DW

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ