1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አቃቤ ህግ የከሰሳቸው ሙስሊሞች

ሐሙስ፣ ነሐሴ 21 2007

ተከሳሾቹ ፣ከዚህ ቀደም በፀረ ሽብር ህግ የተከሰሱ የሙስሊሞችን መፋትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን በአመፅና በብጥብጥ ለማስፈታት እንዲሁም መንግሥትን በኃይል አስወግዶ እስላማዊ መንግሥት ለመመሥረት አሲረዋል በሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል ።

https://p.dw.com/p/1GMzh
Waage der Göttin Justitia
ምስል dpa

[No title]


የፌደራል አቃቤ ህግ በፀረ ሽብር ህግ በእነ አቡበከር መሐመድ መዝገብ 20 ሙስሊሞችን ከሷል። አብዛኛዎቹ ወጣቶች የሆኑት እነዚሁ ተከሳሾች ፣ከዚህ ቀደም በፀረ ሽብር ህግ የተከሰሱ የሙስሊሞችን መፋትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን በአመፅና በብጥብጥ ለማስፈታት እንዲሁም መንግሥትን በኃይል አስወግዶ እስላማዊ መንግሥት ለመመሥረት አሲረዋል በሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል ። ችሎቱ ዛሬ የተከሳሾችን የመቃወሚያ ሃሳብ በፅሁፍ ተቀብሎ ጉዳዩን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለመስከረም 4 2008 ዓም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ። የዛሬውን ችሎት የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር ተከታትሎታል።


ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ