1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አበሻ ኤጀንሲ ሊቢያ የሚገኙ ስደተኞች ና UNHCR

ሐሙስ፣ መጋቢት 22 2003

ከሳምንታት በፊት ከተቀሰቀሰው በሊቢያው ጦርነት ምክንያት በርካታ ስደተኞች መውጫ አጥተው እንደሚሰቃዩ በየአጋጣሚው ይናገራሉ ። ዶቼቬለ በተለያዩ ጊዜያት ያነጋገራቸው ሊቢያ ያሉ ኢትዮጵያውያን በሞት እና በህይወት መካከል እንደሚገኙ እና አብዛኛዎቹም ተስፋ ወደ መቁረጥ መድረሳቸውን ነው የሚገልፁት ።

https://p.dw.com/p/REK5
ምስል picture-alliance/dpa

ሊቢያ ከነበሩት ኢትዮጵያውያን ኤርትራውያንና የሶማሌ ስደተኞች ውስጥ የተወሰኑት ግን አበሻ ኤጀንሲ በተባለው ግብረ ሰናይ ድርጅት ድጋፍ በልዩ ልዩ ጊዜያት ወደ ኢጣልያ መግባት ችለዋል ። በዚህ ድርጅት እገዛ እና ማሳሰቢያ ከሊቢያ ግጭት በኋላ 110 ሰዎች በአየር ወደ 1500 ደግሞ በባህር ኢጣልያ መግባት መቻላቸውን የድርጅቱ ሃላፊና መሥራች አባ ሙሴ ዘራይ ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ። ከሊቢያ የተለያዩ ከተሞች መውጣት ስለተሳናቸው ሌሎች ስደተኞች እና ድርጅታቸው ስለሚያደርግላቸው እገዛ አባ ሙሴን በስልክ ጠይቄያቸዋለሁ ። ተሳክቶላቸው ኢጣልያ መግባት የቻሉት ስደተኞች በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ በቅድሚያ ይገልፁልናል ። የሊቢያ ስደተኞችና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የሊቢያው ጦርነትና በዚያ የሚገኙ ስደተኞች ሁኔታ አሁንም እንዳነጋገረ ነው ። ብራሰልስ ቤልጅየም በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የአውሮፓ ህብረት የስደተኞች መልሶ ማቋቋም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን በታሰበበት በትናንትናው ዕለት በሊቢያ የሚገኙ ስደተኞች ጉዳይ ተነስቶ ነበር ። የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ በዚሁ ስብሰባ ላይ የተገኙትን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን UNHCR እና በአውሮፓ ህብረት የአሜሪካን የስደተኞች ጉዳይ ተወካይን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራል ።

ገበያው ንጉሤ

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ