1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አባ ዉዴ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 12 2000

ወፍ ጭጭ ሳይል ጨለማዉ ለቀቅ ማድረግ ሲጀምር ሰዉ ሳያያቸዉ ከቤት ቤት የሚለምኑትን ሰዎች በተለያየ አካባቢ የተለያየ ስም ተሰጥቶአቸዉ እናገኛለን። በትግራይ ሃሚን፣ በጎንደር አሚና ወይም አባ ነዝንዝ፣ በጎጃም አሚና፣ በወሎ አባዉዴ፣ በሸዋ እና በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ ላሊበላ ይባላሉ።

https://p.dw.com/p/E8Ev

ሃሚና ፣ አሚና ፣ አባ ዉዴ ፣ አባ ነዝንዝ ወይም ላሊበላ የሚባሉት ሰዎች እነ ማን ናቸዉ፣ ካልለመንን ቁምጥና በሽታ ይይዘናል የሚል እምነት እንዳላቸዉም ይነገራል፣ እርግማናቸዉ ይደርሳል ስለሚባልም በህብረተሰብ ዘንድ ይፈራሉ፣ ይከበራሉ፣ እዉነት ይህ የልመና ስርአት ከባህል ይመደብ ይሆን? አሁን አሁን የኔብጤዉን ከሃሚናዎች መለየት ያስቸግራል፣ በሌላ በኩል የቁምጥና በሽታ መድሃኒት ተገኝቶለታል! በዚህም ምክንያት ይህ አይነቱ የልመና ስርአት የጠፋ ይመስላል የሚሉም አሉ። የእነዚህ ወገኖች ታሪክ ምን ይመስል ይሆን ባለሞያ አነጋግረናል መልካም ቆይታ