1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አቶ ካኽሳይ በርኸ ተቀበሩ

ሐሙስ፣ ኅዳር 22 2009

ከሕዝባዊ ወያኔ ትግራዊ ማለትም ሕወሃት መሥራቾች ከነበሩት አንዱ የአቶ ሕኽሳይ በርሀ የቀብር ሥርዓት በዛሬ ዕለት ትግራይ ሰለኽላኻ ዉስጥ ተፈጸመ። አቶ ካሕሳይ ኅዳር 11 ቀን እዚህ ጀርመን ሀገር በሙንስተር የዩኒቨርሲቲ ክሊኒክ ለአንድ ወር ያህል በህክምና ሲረዱ ቆይተዉ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸዉ ተሰምቷል።

https://p.dw.com/p/2Tate
Kahsai Berhe TPLF
ምስል privat

Beri. Berlin (Kahsai Berhe Nachruf) - MP3-Stereo

 በቅርብ የሚያዉቋቸዉ ለዶቼ ቬለ እንደገለፁት አቶ ካሕሳይ 11 ሆነዉ ወደ ደደቢት ተራራ በመጓዝ የትጥቅ ትግል ከጀመሩት የትግራይ ነፃ አዉጭ ቡድን መሥራቾች አንዱ የነበሩ ሲሆን፤ ለረዥም ዓመታት በስደት ሕይወታቸዉን ሲገፉ ቆይተዋል። በዘገባዉ ከሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ መሥራቾች አንዱ ዶክተር አረጋዊ በርሄ ፣ አቶ ካህሳይ በርሀ ከድርጅቱ እንዲባረሩ ያደረጉት የቀድሞ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም መስፍን ናቸው ሲሉ ስለገለፁት፤ ከአምባሳደር ስዩም ወይም ከሕወሀት አስተያየት ለማግኘት ሞክረን ነበር ። ቤይጂንግ ስንደውል አምባሳደር ስዩም ኢትዮጵያ መሆናቸው ተነግሮን በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲሁም በህዝብ ግንኙነታቸው በኩል ርሳቸውን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም ። የሕወሀት ሃላፊዎችንም በስልክ ማግኘት አልቻልንም ። ጥረታችን ግን ይቀጥላል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ