1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አነጋጋሪዉ የኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይ

እሑድ፣ መጋቢት 11 2008

የኢትዮጵያ እና ሱዳን መንግሥታት የድንበር ማካለል ስምምነት ላይ መድረሳቸዉ በተለያዩ ጊዜያት ሲነሳ የቆየ ጉዳይ ነዉ። ይካለላል የሚባለዉ አካባቢ ከአንድ ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ አንዳንዴም ከ700 ኪሎ ሜትር በላይ እንደሚሆን ሱዳን ትሪቢዮን የተሰኘዉ የዜና አዉታር በተደጋጋሚ ዘግቧል።

https://p.dw.com/p/1IG6G
Karte Sudan Südsudan mit Abyei Englisch

አነጋጋሪዉ የኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይ

የዜና ምንጩ በቅርቡ ደግሞ ድንበሩን ለማካለል የተሰየመዉ የቴክኒክ ኮሚቴ የተባለዉን የያዝነዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት ከማለቁ በፊት ተግባራዊ ለማድረግ መዘጋጀቱን ማስታወቁን የኮሚቴዉን ሰብሳቢ ጠቅሶ አስነብቧል። ይሁንና ከኢትዮጵያም ሆነ ከሱዳን መንግሥት በኩል በይፋ የተነገረ ነገር የለም። የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት በምክር ቤት ደረጃ የተባለዉን እንዳልተጀመረ፤ የሚደረግ ከሆነም ህዝቡን አማክረዉ እንደሚሆን ተናግረዋል። በትክክል በሁለቱ ሃገራት መካከል ስለሚነገረዉ የድንበር ማካለል ጉዳይ ያለዉ ተጨባጭ ነገር ምን ይመስላል? ዉይይቱን በድምጽ ያገኙታል።

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ