1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

Merga Yonas Bula
ሰኞ፣ ሚያዝያ 30 2009

የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት አንቀፅ 49 ንዑስ አንቀጽ 5 የኦሮምያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ ያለዉን «ልዩ ጥቅም» በጥቅሉ ይጠቅሳል።

https://p.dw.com/p/2ccMc
Addis Ababa (Äthiopien)
ምስል picture alliance/landov

Detabing the Special Interest Addis Abeba - MP3-Stereo

ይህም ኦሮምያ በአዲስ አበባ ላይ የማኅበራዊ አገልግሎት የማገኘት፣ የተፈጥሮ ሃብትን የመጠቀምንና የጋራ አስተዳደር ጉዳዮች ሊከበርለት እንደሚገባ ይደነግጋል። ዝርዝሩም በአዋጅ እንደምወጣ አስቀምጠዋል። ይሁን እንጅ ይህ ሳይሆን በመቅረቱ እስካሁን የግጭቶች መንሴ እንዲሁም የመወያያ ርዕስ ሆኖ ቀጥለዋል። ሰሞኑን በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የኦሮሚያን «ልዩ ጥቅም የሚያስጠብቅ» የተባለ ረቅቅ አዋጅ «ሾልኮ» ወጥቷል በሚል የተሰራጨዉ ሰነድ ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል።

የአገሪሩ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙለቱ ተሾመ ይህን «ልዩ ጥቅም» የሚያስጠብቅ የሕግ ማእቀፍ እንደሚወጣ  በፓርላማ መክፈቻ ንግግራቸዉ ጠቅሰዉ ነበር። «ፕሬዚዳንቱ  በመስከረም ወር ያደረጉት ንግግር ለአንድ ዓመት ስለሚቆይ በቀረዉ ግዜ ዉስጥ ስለ ልዩ ጥቅሙ  ዝርዝር የያዘ አዋጅ ለማዉጣት መንግስት አስፈላጊዉን ዝግጅት እያደረገ  መሆኑን  በመንግስት ኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስቴር ዲየታ አቶ ዛዲግ አብረሃ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።

የፌዴራሉም ሆነ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኮሙኒኬሼን ጽ/ቤት ይህ «ሾልኮ» ወጣ የተባለዉን ረቅቅ አዋጅ እነሱ እንደማያዉቁ መነገራቸዉን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ለዶይቼ ቬሌ ይናገራሉ። «ሾልኮ ወጣ» የተባለዉን ረቂቅ አዋጅ እንዳላገኙም ተናግረዋል።

እስካሁን ይህ «ልዩ ጥቅም» ተፈጻሚ ያልሆነበት ምክንያት ክልሉን የሚያስተዳድር መንግስት ስራዉን ስላልተወጣ ነዉ ሲሉ አቶ ሙላቱ ገልፀዋል።

በአገሪቱ የነበረዉ ተቃዉሞ ጥንስሱ የአዲስ አበባንና የኦሮሚያ ልዩ ዞንን በ«ልማት» ማስተሳሰር ማስተር ፕላን መሆኑ ይታወሳል። ይሁን እንጅ በ«ልማት ስም» ገበሬዎች ከቄያቸዉ እየተፈናቀሉ እንደሚገኙ፣ ተገቢ ማህበራዊ አገልግሎት እያገኙ እንዳልሆነ፣ ባሕላቸዉንና ቋንቋቸዉ እየተገፋ ይገኛል የሚል ተቃዉሞዉን ማባባስ መቻሉን ዘገባዎች ያመለክታሉ።

«ሕገ መንግስቱ የሕጎች ሁሉ አባት ነዉ» የሚሉት አቶ ሙላቱ ገመቹ መንግስት በሕገ መንግስቱ የተደነገገዉን አንቀፅ  ማስፈፀም እንደሚገባና ሰላማዊ ትግል ማስከበር እንዳለበት ተናግረዋል።

 

መርጋ ዮናስ

አዜብ ታደሰ