1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አነጋጋሪዉ የዋልድባ ገዳም ህልዉና

ሐሙስ፣ ሐምሌ 12 2004

ካለፈዉ መጋቢት ወር አንስቶ ለስኳር ልማት ፕሮጀክት ሲባል ጥንታዊዉ የዋልድባ ገዳምን ይዞታ ይነካል በሚል የተለያዩ ወገኖች ስጋታቸዉን ሲገልፁ ተደምጠዋል። ፕሮጀክቱን የሚመራዉ የመንግስት አካል በበኩሉ የተጠቀሰዉ ፕሮጀክት የገዳሙን ዋነኛ ክፍል

https://p.dw.com/p/15bAw
ምስል picture alliance/imagestate/Impact Photos

 እንደማይነካ ነዉ የተናገሩት። ሰሞኑን  ደግሞ ይህ ፕሮጀክት የገዳሙን አካል ይነካል የሚል ስጋታቸዉን ለመገናኛ ብዙሃን ካስደመጡ  የገዳሙ መነኮሳት አንዱ ለእስር መዳረጋቸዉ፤ ገዳሙም ዉስጥ ወታደሮች መገኘታቸዉ ይነገራል። ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከፍተኛ አካል ስጋታችንን ብንገልፅም ምላሽ አላገኘንም የሚሉት በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች እና ምዕመናን ዛሬ ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ ፍራንክፈርት ከተማ ላይ ሰልፍ አካሂደዋል።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ