1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አነጋጋሪው የጉዲፈቻ ጉዳይ

ሰኞ፣ መስከረም 11 2002

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በርካታ ኢትዮጵያውያን ህፃናት በጉዲፈቻ ወደ በለፀጉት አገራት እየተወሰዱ ነው ። በተለይም በዚህ መንገድ ወደ አሜሪካን የሚሄዱት ህፃናት ቁጥር ከዛሬ አራት ዓመት ወዲህ በአራት ዕጥፍ መጨመሩ ይነገራል ።

https://p.dw.com/p/Jlli
ምስል UNO

ህፃናት ከኢትዮጵያ በማደጎ ወደ በለፀጉ ሀገራት የሚሄዱበት መንገድና ከተወሰዱ በኃላም መደረግ የሚገባው ክትትል አነጋጋሪ ከሆነ ሰነባብቷል ። አንዳንድ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች እንደሚሉት በዚህ ተግባር ውስጥ መስናና ማጭበርበር ስር ሰዷል ። በጉደፈቻ ከኢትዮጵያ የሚወጡ ህፃናት ጉዳይ የሚመለከተው የኢትዮጵያ የሴቶችና የህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ በዚህ ረገድ ከህግ ውጭ የሚከናወን ነገር የለም ሲል ያስተባብላል ። እስካሁን የጎላ ችግር አላጋጥመም የሚለው ሚኒሴቴር መስሪያ ቤቱ በጉዲፈቻ ወደ ውጭ የሚላኩ ህፃናትን መስሪያ ቤቱ እንደሚከታተል አስታውቋል ።

ታደሰ እንግዳው ፣ሒሩት መለሰ፣ ሸዋዬ ለገሠ