1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አካባቢን ለመከባከብ የኅብረተሰብ ጥረት

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 20 2003

የደን ሃብት በኢትዮጵያ እየተመናመ በመሄድ ላይ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ደጋግመዉ ያሳስባሉ።

https://p.dw.com/p/RKxF
ምስል picture-alliance / dpa

በሃረማያ ሐይቅ ላይ የገጠመዉ የመድረቅ አደጋም በስምጥ ሸለቆ አካባቢ በሚገኙ ሐይቆች ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ እያንዣበበ መሆኑን ጥናት ያካሄዱ ባለሙያ በሳምንታዊ ጤናና አካባቢ ዝግጅታችን ቀርበዉ ማብራራታቸዉ ይታወሳል። በኦሮሚያ ክልል ፤ በምሥራቅ ሸዋ ፣ ጋሎ አረጲ በተባለ ሥፍራ የተፈጥሮ አካባቢን መራቆት ለመቋቋም፣ ኅብረተሰቡ የሚያደርገውን ጥረት ፣ እንዲሁም ድርቅ በዐቢያታ ሀይቅ ላይ ያስከተለውን ከባድ ተጽእኖ ከሰሞኑ ተመልክቶ የተመለሰው የአዲስ አበባው ዘጋቢአችን ጌታቸው ተድላ፣ የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።