1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

አወዛጋቢዉ የኢኮኖሚ ትንበያ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 2 2009

ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪቃ  የኢኮኖሚ መሪነትን  በመጪዉ ዓመት ከኬንያ እንደምትረከብ አለም አቀፉ የገንዘብ ተቁዋም በምህፃሩ አይ ኤም ኤፍ ከሰሞኑ ባወጣዉ የትንበያ ዘገባዉ አመልክቷል። ተቋሙ በዘገባዉ የኢትዮጵያን የዉጭ  የቀጥታ መዋእለ-ንዋይ ፍሰትን ለትንበያዉ መነሻ ካደረጋቸዉ  መስፈርቶች ዉስጥ አንዱ መሆኑን ጠቅሷል።

https://p.dw.com/p/2RATB
Proteste in Äthiopien abgebranntes Auto
ምስል Reuters/T. Negeri

የአይ ኤም ኤፍ የኢኮኖሚ ትንበያ

ኢትዮጵያ በመጪዉ ዓመት በምስራቅ አፍሪቃ የኢኮኖሚ መሪነትን ከኬንያ እንደምትረከብ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቁዋም በምህፃሩ አይ ኤም ኤፍ ከሰሞኑ ባወጣዉ የትንበያ ዘገባዉ አመልክቷል። ይሁን እንጅ በሃገሪቱ ለወራት እየተካሄደ ያለዉ ሕዝባዊ ተቃዉሞ በተለያዩ ዘርፎች  የተሰማሩ የዉጭ ኩባንያወች  የጥቃት ኢላማ እየሆኑ መምጣት የተቋሙን የኢኮኖሚ ትንበያ  አወዛጋቢ እንደሚያደርገዉ  የኢኮኖሚ ባለሙያወች  ገልጿል። 

ኢትዮጵያ  በአፍሪካ  ጥሩ የኢኮኖሚ  መሻሻል  አያሳዩ ነው  ከሚባሉ ሀገሮች  ወስጥ ስሟ  በለም አቀፉ  የገንዘብ ተቁም  በምህፃሩ  አይ አም  አፍ   ሰሞኑን ባወጣዉ  ዘገባ ተጠቅሷል ።  ተቁሙ  የአፍሪካን የአኮኖሚ  ጉዳዮች በተመለከተበት  ዘገባዉ የመሰረተ ልማት ዝረጋታን በሀገሪቱ አየተሰሩ  ያሉ  የትልልቅ  ፕሮጀክቶችንና የዉጭ  የቀጥታ መዋአለ  ንዋይ  ፍሰትን   አንደመመዘኛ  ወስዶ  ትንበያዉን ያወጣ ሲሆን ባለፉት ሁለት አስረተ ዓመታት ተገኘ የተባለዉን ባለዉን ባለ  ሁለት  አሃዝ የኢኮኖሚ እድገትና የሀገር ዉስጥ ጠቅላላ ምርት እድገትን መነሻ በማድረግም በመጭዉ ዓመት የምስራቅ አፍሪካን ትልቅ የኢኮኖሚ ባለቤትነት ከኬንያ እንደምትረከብ ተቁሙ በዘገባዉ አስቀምጧል። በአሜሪካን ሀገር  የሚገኘዉ ሲስካንሰን ዩንቨርስቲ ያኢኮኖሚክስ  መምህርና  በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ምርምር ያካሄዱት  ፕሮፌሰር ዳንአል ተፈራ ግን በዚህ አይስማሙም ። እሳቸዉ እንደሚሉት ዘገባዉ የአበዳሪ ተቁማት የተለመደ ሙገሳ ነዉ።

ሀገሪቱ በምትከተለዉ ግብርና መር ኢንደስትሪ ፖሊስ መሰረት በአበባ ምርት በጨርቃጨርቅ በቆዳ ዉጤቶች በአትክልትና ፍራፍሬ  እንዲሁም በሌሎች  ዘርፎች  የሀገር ዉስጥና የዉጭ ባለሀብቶች ተሰማርዉ  ይገኛሉ። እነዚህ ባለሀብቶች  ነፃ ና ርካሽ  መሬትና አገልግሎት እንዲሁም የገንዘብ ብድር ከመንግስት በማግኘት ባለፉት ሁለት አስርተ አመታት እስከ ሁለት ቢሊዮን ዶላር  የሚደርስ መዋለ ንዋይ እንዳፈሰሱ መንግስት ሲገልፅ  ቆይቷል። እንደ   ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቁም ትንበያም   ከሀገሪቱ የዉስጥ ምርት እድገት አንፃር  የቀጥታ የዉጭ መዋዕለ ንዋይ ፍሰት ሰላሳ ዘጠኝ ነጥብ ሁለት  በመቶ ድርሻ ይኖረዋል በሚል ትንበያዉን ያስቀመጠ ሲሆን ለኢኮኖሚ እድገት ያለዉን ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ በዘገባዉ ተጠቅሷል።ፕሮፌሰር ዳንኤል ይቀጥላሉ።

Äthiopien Addis Ababa - Neuer Zug verbindet Hafen und Stadtzentrum
ምስል picture-alliance/Photoshot/Xinhua/S. Ruibo

አንዳንድ የኢኮኖሚ ተንታኞች ግን የሀገሪቱ ኢኮኖሚ እድገትም ሆነ ከመዋእለ ንዋይ ፍሰት የሚገኘዉ ጥቅም የሚወሰነዉ መንግስት  የህዝቡን ጥያቄ በተገቢዉ መንገድ በመመለስ በሃገሪቱ  በሚያሰፍነዉ ዘላቂ ሰላምና የተረጋጋ ገበያ ሲፈጠር ብቻ ነዉ የሚሉት ፤ ያ ካልሆነ  ግን የሚታሰበዉ ያኢኮኖሚ እድገትም ሆነ የተቁሙ ትንበያ  ዋጋ የለዉም ነዉ የሚ,ሉት ባለሙያወቹ። ለዚህም እንደ ማሳያ እየተወሰደ ያለዉ ካለፈዉ ህዳር ወር ጀምሮ በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች እየተካሄደ ያለዉ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ  አሁን አሁን የሀገር ዉስጥና የዉጭ ኩባንያወች የተቃዉሞ ኢላማ እየሆኑ መምጣታቸዉ ነዉ። የፖለትካ ችግር  በአግባቡ ካልተፈታ የኢኮኖሚ ችግር እንደሚያስከትል   የኢኮኖሚ ባለሙያዉ ፕሮፌሰር ዳንኤል ተፈራ ይናገራሉ።
   

በተቃዉሞ እንቅስቃሴዉ የሆላንድ የአበባ እርሻ ፣የቱርክ የጨርቃጨርቅ  ፋብሪካ  ፣የናይጄሪያ ስሚንቶ ፋብሪካ፣ኢስማላ የአበባ እርሻና ሌሎችም የንብረት ዉድመት ደርሶባቸዋል።በጉዳቱ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ኪሳራ እንደደረሰባቸዉ የተለያዩ ዘገባወች ያመለክታሉ።ይህንን ።ተከትሎም መንግስት የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጅ አዉጥቶአል።ለመሆኑ በሀገሪቱ
ኢኮኖሚ የሚኖረዉ ተፅኖ ምንድነዉ? ፕሮፌሰር ዳንኤል ተፈራ ያብራራሉ።

ፀሐይ ጫኔ

ነጋሽ መሐመድ