አወዛጋቢው የአልሲሲ የጀርመን ጉብኝት
ሐሙስ፣ ግንቦት 27 2007ማስታወቂያ
የግብጹ ፕሬዝዳንት የአብዱል ፈታህ አል ሲሲ የጀርመን ጉብኝት እያወዛገበ ነው ። ሃገራት የሰብዓዊ መብት እንዲያከብሩ አበክራ የምታሳስበው ጀርመን በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የታሰሩባት ሙት በቃ ብይን የሚወሰንባትና የሚፈፀምባት ሃገር መሪን በእንግድነት መጋበዟ ከውጭም ከሃገር ውስጥም ተቃውሞ አስነስቷል ።የጀርመን ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ኖርቤርት ላሜርት ግብፅ ውስጥ በሚፈፀሙት ልዩ ልዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ምክንያት አል ሲሲን እንደማያነጋግሩ አስታውቀዋል ። አንዳንድ ፖለቲከኞች ደግሞ ግብፅ ውስጥ ዲሞክራሲ ሙሉ በሙሉ ከመስፈኑ በፊት የግብፁ መሪ በጀርመን ለይፋ ጉብኝት ባይጋበዙ ይሻል ነበር ሲሉም ተደምጠዋል ።ስለ አልሲሲ የጀርመን ጉብኝት የበርሊኑን ወኪላችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ