1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዉሮጳን ያጥለቀለቀዉ የስደተኛ ጎርፍ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 28 2007

አዉሮጳን ያጥለቀለቀዉ የስደተኞች ጎርፍ የአዉሮጳ ኅብረትን አንድነት አናዉጦ የተመሠረተባቸዉን እሴቶችና መርሆዎችን ጥያቄ ዉስጥ እያስገባ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1GQlA
Belgien Donald Tusk und Viktor Orban EU Parlament Brüssel
ምስል picture-alliance/dpa/O. Hoslet

[No title]

ከጦርነትና እልቂት አምልጠዉ ተገን ፍለጋ አዉሮጳ የሚገቡት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩት ስደተኞች በርካታ በሚባሉ የአዉሮጳ መንግሥታት እንደስጋት ተቆጥረዉ በር ተዘግቶባቸዋል። ዛሬ አዉሮጳ በየቀኑ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞች እምቢ ብለዉ የሚገቡባት ብቻ ሳትሆን የሕፃናት አስከሬን ከባህር ሲለቀም፤ ብዙዎችም በተሽከርካሪ ታጭቀዉ ሕይወታቸዉ ሲያልፍ፤ ሌሎች ደግሞ በባቡር ተገጭተዉ ሲሞቱና ሲቆስሉ የሚታዩባት የሰቆቃ ምድር ሆናለች። የብራስልስ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤ ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ