1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዉሮጳ በብራስልስ ሽብር ማግሥት

ረቡዕ፣ መጋቢት 14 2008

የቤልጅግ ሕዝብ ትናንት በሐገሪቱን ርዕሠ-ከተማ ብራስልስ በደረሰዉ የአሸባሪዎች ጥቃት የተገደሉ ወገኖቻቸዉን ዛሬ አስበዉ ዋሉ። የቤልጂግ መንግሥት በመላዉ ሐገሪቱ የሚፀና የሰወስት ቀን ብሔራዊ ሐዘን አዉጇል።

https://p.dw.com/p/1IILe
ምስል Getty Images/AFP/K. Tribouillard

[No title]

ትናንት ብብራስልስ አዉሮፕላን ማረፊያ እና በአንድ የምድር ዉስጥ ባቡር ጣቢያ በደረሰ ፍንዳታ በትንሹ ሰላሳ-አንድ ሰዎች ተገድለዋል። ከ250 በላይ ቆስለዋል ። ቦምቡን ካፈነዱት መካከል ሁለቱ በፍንዳታዉ ሲሞቱ ሰወስተኛዉ አሁንም እንደተሰወረ ነዉ። የአዉሮጳ ከተሞች በተደጋጋሚ በአሸባሪዎች መጠቃታቸዉ ዳግም የመነጋገሪያ ርዕሥ ሆኗል።

የቤልጅግዋ ርዕሰ-ከተማ ብራስልስ ትናንት በአሸባሪዎች ከተጠቃኝ ወዲሕ እዚያዉ ቤልጂግ እና በአጎራባቾችዋ ሐገራት የሚደረገዉ የፀጥታ ጥበቃ እና ቁጥጥር ዛሬም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነዉ። ከፍተኛ ቁጥጥር ከሚደረግባቸዉ ሐገራት አንዷ ጀርመን ናት። የጀርመን ፀጥታ አስከባሪዎች በተለይ ሐገሪቱን ከቤልጂግ፤ ከፈረንሳይ፤ ከኔዘርላንድስ እና ሉክስምቡርግ ጋር የሚያዋስኑ ድንበሮችን በጥብቅ እየፈተቆጣጠሩ ነዉ። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል እንደታዘበዉ ደግሞ አዉሮፕላን ማረፊያዎች፤ባቡር ጣቢያዎች፤ ሕዝብ የሚያዘወትራቸዉ የገበያ ማዕከላትም ባይነ ቁራኛ እየተጠበቁ ነዉ።

Belgien Schweigeminute EU Brüssel
ምስል Reuters/F. Lenoir

ገበያዉ ንጉሴ

ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ