1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዉሮፕላንና ከባቢ አየር

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 28 2001

ለዓለም የከባቢ አየር ሙቀት መጨመር ሰበብ የሆኑትን አደገኛ ጋዞች ከሚለቁ ግዙፍ ኢንዱስትሪዎች ባላነሰ የአየር ላይ መጓጓዣም ተጠያቂ መሆኑ ማነጋገር ከጀመረ ሰንብቷል።

https://p.dw.com/p/GSzO
...በፅዱ ቴክኒዎሎጂ ይተኩ...
...በፅዱ ቴክኒዎሎጂ ይተኩ...ምስል picture-alliance / dpa/dpaweb

መፍትሄ የተባሉ ሃሳቦችም እየቀረቡ ነዉ። ነገሩ ሲታሰብ ቀላል ቢመስልም ከመቶና ሁለት መቶ በላይ ሰዎችን በአየር ላይ ለማንሳፈፍና ካሰቡበት በሰላም ለማድረስ ቴክኒዎሎጂዉ ሲፈጠር ጊዜ እንደፈጀ ሁሉ፤ እድገቱን ለማሻሻልም ጊዜ መጠየቁ ግድ ነዉ። ጅምሩና ሙከራዉ ግን ተስፋ ይሰጣል። ነገን የተሻለ ለማድረግ ጥረት ወሳኝ ነዉና።