1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አውሮፓ በጎሮጎሮሳውያኑ 2010 ዓም

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 19 2003

ሊሰናበት 3 ቀናት ብቻ በቀረው በጎርጎሮሳውያኑ 2010 ዓም በአውሮፓ ክፍለ ዓለም የሚታወሱ ዓበይት ክስተቶች ናቸው የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት አብረን እንቆይ ።

https://p.dw.com/p/QkkI
ቤልጂጋዊው ፋን ሮምፖይምስል AP

አውሮፓ በ 2010 የተጠበቁም ያልተጠበቁም ክስተቶችን አስተናግዳለች ። አመቱ በገንዘብ ቀውስ ሰበብ ኪሳራ አፋፍ ላይ የቆሙ አገራትን ከውድቀት የማዳን ዕርምጃዎች ላይ የተተኮረበት ፣ ምጣኔ ሐብታቸው ሲንገዳገድ የስራ አጡ ቁጥር የጨመረባቸው ሐገራት ከመቼውም ጊዜ በተጠናከረ ሁኔታ ድንበራቸውን አጥብቀው በመዝጋታቸው ስደተኞች የተንገላቱበት ፣ ያልታሰቡ ውጤቶችን ያስከተሉ ምርጫዎች የተካሄዱበት ፣ ዓመት ነበር ።

ሂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ