1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሱ የመንግሥት ቃል አቀባይ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 23 2009

በትናንትናዉ ዕለት የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 21 አዲስ ተሿሚዎችን ሚኒስትርነት አጽድቋል።

https://p.dw.com/p/2S32R
Äthiopien Addis Abeba Vereidigung Kabinett
ምስል Imago/Xinhua

Excl. Interview with Dr. Negeri Lenco - MP3-Stereo


ከአዲሶቹ ዉስጥም በአዲስ አበባ ዩኒቨሲቲ ለቋንቋዎች ጥናት ተቋም በምክትል ዲን እንዲሁም ለየጋዜጠኝነት እና ኮሙኒኬሽን ተቋም የደህረ ምረቃ መርሃ ግብር አስተባባር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ በአቶ ጌታቸዉ ረዳ ሲመራ የነበረዉን የመንግሥት ኮሙኒኬሼን ሚንሥቴር እንዲመሩ ተሹመዋል።

በምዕራብ ኦሮሚያ ዳሌ ዋባራ የተባለችዉ ወረዳ የተወለዱት ዶክተር ነገሪ ሌንጮ በመጀመርያ ደረጃ ትምህርታቸዉ ስኬታማ እንደነበሩ ይናገራሉ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸዉን በቀለም ወላጋ በደምብ ዶሎ ከተማ በታዋቂዉ ቤቴል ወንጌላዉያን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል። ከዚያም የእንግሊዝኛ ቋንቋና ስነፁሁፍን በኮተቤ መምህራን ማስልጠኛ ኮሌጅ ተምረዋል። 


በ1992 በኦሮሚያ ባህልና ማስታወቂያ ተቀጥረዉ ለሁለት ዓመት ተኩል ከሠሩ በኋላም ባገኙት የትምህርት ዕድል ወደ ሕንድ ሀገር ሄደዉ ሁለተኛ ዲግሪያቸዉን በሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ላይ ሠርተዋል።  የዶክትሬት ትምህርታቸዉንም እዛዉ ሕንድ አንዲራ ዩኒቨርሲቲ በጋዜጠኝነት እና ኮሙኒኬሽን መሥራታቸዉንም ይገልጻሉ። ትናንት በተደረገዉ የባለስልጣናት ሹም ሽርን አስመልክቶ አነጋግሬያቸዋለሁ።  

መርጋ ዮናስ

አዜብ ታደሰ