1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሱ የሶማሊያ ዜና አገልግሎት

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 22 2001

SOMINA ከሶማሊያ የሚያሰባስበዉን መረጃ በሶማሊያኛ፥ በእንግሊዝኛ እና በሌሎችም ቋንቋዎች ለራስዋ ለሶማሊያና ለአለም አቀፍ መገናኛ ዘዴዎች ያሰራጫል

https://p.dw.com/p/Hhdu
SOMINA-እንዲመሠረት ከረዱት ያንዱ አርማ

የሶማሊያን ወቅታዊ ሁኔታ እየተከታተለ ለተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች ዜና የሚያሰራጭ ገለልተኛ የዜና አገልግሎት ተቋም ትናንት ጀቡቲ ዉስጥ ተከፈተ።SOMINA በሚል የእንግሊዝኛ ምሕፃረ-ቃል የሚጠራዉ ተቋም ከሶማሊያ የሚያሰባስበዉን መረጃ በሶማሊያኛ፥ በእንግሊዝኛ እና በሌሎችም ቋንቋዎች ለራስዋ ለሶማሊያና ለአለም አቀፍ መገናኛ ዘዴዎች ያሰራጫል።በሶማሊያዉያን ጋዜጠኞች የሚመራዉን ተቋም ፓሪስ የሚገኘዉ ጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት-ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች፥ ዶሐ-ቀጠር የሚገኘዉ ለመገናኛ ዘዴዎች ነፃነት የሚሟገተዉ-ማዕከልና በሶማሊያ ጋዜጠኞች ሕብረት የሚረዳ ነዉ።ነጋሽ መሐመድ ዝር ዝሩን አጠናቅሮታል።

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ