1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሱ የተ.መ.ድ. ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ 

ሰኞ፣ ጥቅምት 7 2009

የቀድሞው የፖርቹጋል ጠቅላይ ሚኒሥትር አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የዓለም ከፍተኛው ዲፕሎማት ሆነው በመጪው ጥር ባንኪ ሙንን ይተካሉ።

https://p.dw.com/p/2RLno
Portugal Lissabon Antonio Guterres
ምስል picture-alliance/AP Photo/S. Govern

Portugal's Antonio Guterres elected UN secretary-general - MP3-Stereo

የ67 ዓመቱ ጉቴሬዝ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን በምሕፃሩ (UNHCR) ዋና ኃላፊ ሆነው ለ10 ዓመታት አገልግለዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ ለመሆን ከ13 እጩዎች ጋር የተወዳደሩት ጉቴሬዝ ባለፈው ሐሙስ በይፋ ሹመታቸውን ተቀብለዋል። በዕለቱ በኒው ዮርክ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ባደረጉት ንግግር ስሜታቸውን «ምሥጋና» እና «ትኅትና» የሚሉት ቃላት እንደሚገልጡት ተናግረዋል። በበርካታ ጉዳዮች ላይ የማይስማሙት ዩናይትድ ስቴትስ እና ሩሲያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አምባሳደሮቻቸው በኩል ለአንቶኒዮ ጉቴሬዝ ያላቸውን ጠንካራ ድጋፍ ገልጠዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን በዋና ጸሃፊነት መምራት ያለበት እስካሁን እድሉ ካልደረሰው የምዕራብ አውሮጳ ቀጠና መምጣት ይኖርበታል፤እንዲሁም ከስምንት ወንዶች በኋላ አለማቀፋዊው ተቋም በእንስት ይመራ የሚሉ ክርክሮች ከምርጫው በፊት ነበሩ። አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በዕለቱ «ዓለም አደገኛ ጊዜ ከፊቷ ተደቅኗል።» ሲሉ አስጠንቅቀዋል። 
መክብብ ሸዋ 
እሸቴ በቀለ

Portugal's Antonio Guterres elected UN secretary-general - MP3-Stereo