አዲሱ የእስራኤል መንግስት
ረቡዕ፣ መጋቢት 23 2001ማስታወቂያ
ትናንት ልዩ ጉባኤ ያካሄደው የእስራኤል ፓርላማ ክኔሴት ፣ ለነታንያሁ መንግስት 69 የድጋፍና 45 የተቃውሞ ድምፅ ከሰጠ በኃላ ነታንያሁና አዲሱ ካቢኔያቸው ቃለ መሀላ ፈፅመዋል ። ነታንያሁ ለእስራኤል ፓርላማ ባሰሙት ንግግር የእስራኤልን ደህንነት ከማስጠበቅ ጎን ለጎን ከአረቡ ዓለም ጋር ሰላም ለማውረድ እንደሚጥሩ አስታውቀዋል ። ይሁንና በትናንቱ ንግግራቸው ስለ እስራኤልና ፍልስጤማውያን ጎን ለጎን በሁለት መንግስትነት በሰላም ስለመኖር ግን ያሉት የለም
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኃላ