1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

አዲሱ የዚምባብዌ ሸርፍ የፈጠረው ስጋት

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 17 2009

በዚምባብዌ በጣም ብዙ የተለያዩ ሸርፎች አሉ። በዋነኝነት ሰዎች የሚያገለገሉበት ዩኤስ ዶላር ሲሆን፣ ዩሮ፣ የደቡብ አፍሪቃ ራንድ እና የቻይና ዩዋንም ይጠቀሳሉ።  በሀገሪቱ በአሁኑ ጊዜ በጠቅላላ ዘጠኝ የተለያዩ ሸርፎች ይሰራባቸዋል። ያም ሆኖ የገንዘብ ሸርፍ እጥረት ይታያል።

https://p.dw.com/p/2UfHk
Protest Harare Simbabwe
ምስል DW/P.Musvanhiri 

Angst vor Pseudo-Währung in Simbabwe - MP3-Stereo

የሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት ወድቋል፣ ባንኮችም የገንዘብ ኖታ የላቸውም። በመሆኑም፣ መንግሥት ሌላ የራሱ የመክፈያ ዘዴ አስተዋውቋል። ይህ ግን አዲስ ግዙፍ የዋጋ ግሽበት እንዳያስከትል አስግቷል። 
  
ዚምባብዌ ከዚህ ወር ጀምራ በአዲስ ሸርፍ፣ ብሎም፣ በቦንዶች መጠቀም ጀምራለች። በዚህም የተነሳ  የዚምባብዌ ዜጎች መንግሥት በቅርቡ ሀገሪቱን በቦንድ በማጥለቅለቅ ሀገሪቱን ይበልጥ የከፋ ኤኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ ሊከታት ይችላል በሚል ሰግተዋል።  
« ገንዘብ የለም፣ ከዛሬ ጥዋት ጀምሬ ወረፋ ይዤ  እየጠበቅኩ ነው። የባንክ ሰራተኞች አንድም መርረጃ አይሰጡም። ምን እንደሆን የማውቀው ነገር የለም። »
ከወራት ጀምሮ ብዙዎች በባንኮች ደጃፍ እና በገንዘብ ማውጫ ማሽኖች አካባቢ ተሰልፈው የሚታዩበት ሁኔታ የተለመደ ሆኗል። ባንኮችና ማሽኖቹ ባዶ ስለሆኑ  ገንዘብ ከዚሁ ጥበቃ በኋላ ገንዘብ ለማግኘታቸው ዋስትና እንደሌላቸው የቀድሞ የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር  የምጣኔ ሀብት  ቶኒ ሆክንስ አስታውቀዋል። ከአራት እና አምስት ዓመት ወዲህ ግዙፍ  ትልቅ የንግድ ሚዛን ጉድለት ገጥሞናል። ወደ ውጭ ከምንልከው ይበልጥ ወደ ሀገር የምናስገባው ምርት መጠን ይበልጣል። እና የገንዘቡ ዝውውራችን ችግር ላይ ይ ጥሎታል። ከዚህ በላይ ደግሞ ዚምባብዌ ስድስት ቢልዮን የውጭ ዕዳ አለባት፣ በመሆኑም አዲስ ብድር ማግኘቱ አዳጋች ነው። »
ይህ ሁኔታ የፈጠረውን ችግር ለመወጣትም የዚምባባዌ መንግሥት ቦንዶችን አትሞዋል። ከዶላር ጋር አንድ ለአንድ ይመነዘራል፣ በዚህም፣ በገሀድ አዲስ ገንዘብ አውጥታለች ማለት ነው፣ ምንም እንኳን የሀገሪቱ ማዕከላይ ባንክ ኃላፊ ጆን ማንጉድያ አስተባብለዋል። 
« የግምጃ ቤት ሰነዶቹ፣ ማለትም ፣ ቦንዶቹ ምርት ወደ ውጭ  የሚልኩ ተቋማትን ለማበረታታት የታሰቡ ብቻ ናቸው። ሰዉ እነዚህ ሰነዶች በገንዘብ እጥረት ሰበብ የወጡ  መስሎታል። ግን፣ አይደለም። »
መንግሥት መግለጫዎች የሚያደናግሩ ናቸው። ባንድ በኩል ሕዝቡ ቦንዶች መጠቀም አይገደድም ይላል፣ በሌላ በኩል ግን፣ ላጭር ጊዜ መገልገያ ብቻ ነው የወጣው ቢባልም በቀጣይነት በገንዘብነት  እየተሰራበት ባለው ቦንድ የማይጠቀም ሰው በህግ ይቀጣል ይላል። 
ይህ የዚምባብዌን ዜጎች እምነት የሚያገኝ አሰራር አይደለም። ከአስር ዓመት ገደማ በፊት የገንዘብ ኖት የታተመበት ሁኔታ ያስከተለውን መዘዝ፣ ማለትም፣ ግዙፉን ከ200 ሚልዮን ከመቶ በላይ የዋጋ ግሽበት እና ከየዋጋ ውድነትን  በሚገባ ያስታውሳሉ።   የባንክ ሂሳብ ቁጠባ እና የጡረታ ተሰርዟል፣ አንድ ዶላርም ሁለት ቢልዮን ተኩል የዚምባብዌ ዶላር ተዘርዝሯል። በዚያን ጊዜ የታተመው የአንድ መቶ የዚምባብዌ ዶላር ኖት ዘሬም በቱሪስቶች ዘንድ ተወዳጅ ማስታወሻ ነው። የጠንካራው ዶላር መታተም ነው ሁኔታውን ያረጋጋው። በዚህም የተነሳ አዲሱን የመክፈያ ሰነድ ለመቀበል አልፈለጉም።
« የታክሲ ሾፌሩ ዝርዝሩን በቦንድ ሊሰጠኝ ፈለገ። እኔ በዶላር ነው የሰከፈልኩህ አንተም በዶላር መልስልኝ አልኩት። አንድም ቦንድ የመቀበል ሀሳብ በፍጹም የለኝም። »
 በባንክ የተቀመጠ ሂሳብም አሁን ወደ ቦንድ ተቀይሮዋል። መንግሥት ከዜጎቹ ዶላር ወወስዶ በቅርቡ ዋጋቸውን በሚያጡ ማጣታቸው በማይቀር ቦንድ እየተካው ነው።  ይህን አንዳንዶች መውረስ ወይም ግልጽ ስርቆት ብለውታል። በመሆኑም ብዙዎች በየቤታቸው ዶላራቸውን እያከማቹ ነው። 
ሁሉም የዚምባብዌ ዜጎች ግን አይደሉም የገንዘብ እጥረት ያለባቸው። ከፕሬዚደንት ሙጋቤ ጋር ጥሩ ግንኙነት ያላቸው ሀብታሞቹ በሚልዮን የሚቆጠር ዶላር ወደ ውጭ ሳይልኩ እንዳልቀረ ነው የሚነገረው። 

Protest Harare Simbabwe
ምስል DW/P.Musvanhiri 
Afrika Zimbabwe Menschenschlange vor Geldautomat
ምስል Getty Images/AFP/J. Njikizana

ያን ፊሊፕ ሽሊውተር/ አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ