1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሱ የዩኤስ አሜሪካ የሱዳን ፖሊሲ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 10 2002

የዩኤስ አሜሪካ መንግስት በሱዳን አኳያ የሚከተለውን ፖሊሲ መቀየሩን አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/KBFX
የዳርፉር ስደተኞችምስል picture-alliance/ dpa

አዲሱ የዩኤስ አሜሪካ ፖሊሲ ሱዳንን ከማግለል ይልቅ መሰረታዊ ለውጥ እንድታደርግ በማግባባትና በጎ ግንኙነትን በመፍጠር ላይ የሚያተኩር እንደሚሆን ተገልጾዋል። ይህም ቢሆን ግን ለሱዳን ሁሉም ነገር ተመቻችቶዋል ማለት አለመሆኑን ነው የፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ መስተዳድር ያስታወቀው። በተለይ ሱዳን በዳርፉር ያለውን ውዝግብ ለማብቃት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለመተባበር ዝግጁ ካልሆነች ዋሽንግተን ፊትዋን ልታዞርባት እንደምትችል ትናንት የወጣው ሰነድ አመልክቶዋል።

አበበ ፈለቀ/አርያም ተክሌ/ሸዋዬ ለገሰ