አዲስ የስደተኞች መጠላያ ጣቢያ በባየር
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 26 2007ማስታወቂያ
በጀርመን ባየር ግዛት የማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤሚሊያ ሙለር ከምዕራብ ባልካን ሃገራት ለሚመጡ ስደተኞች በጀርመን የመጀመርያና ልዩ የሆነ የስደተኞች መጠለያ ማዕከል መከፈቱን ገለፁ። ባየር ግዛት «ኢንጎልሽታድት» በተሰኘ ከተማ የተከፈተዉ ይህ የስደተኞች መጠለያ ማዕከል በቀድሞ ጊዜ ትልቅ የወታደሮች ሠፈር እንደነበረም ታዉቋል። አዲስ በተከፈተዉ ማዕከል ከደቡባዊ አዉሮጳ የመጡ 500 ያህል ስደተኞች እንደሚኖሩበት ተመልክቶአል። በማዕከሉ ከሚጠለሉት ስደተኞች መካከል አብዛኞቹ በዘላቂነት ጀርመን ዉስጥ የመኖያ ፈቃድ የማያገኙ መሆናቸዉ ተመልክቶአል።እንደ ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ኤሚሊያ ሙለር የስደተኞቹን ጉዳይ የሚያዩ ባለሥልጣን መስርያ ቤቶች በቅርርብ በመሥራት የተገን ጠያቂዎችን ጉዳይ ከአራት እስከ ስድስት ሳምንታት ባለዉ ጊዜ ዉስጥ በማጣራት ፈቃድ ያላገኙ ተገን ጠያቂዎች ወደ ሃገራቸዉ እንዲላኩ ይደረጋል ሲሉ ተናግረዋል።
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ