1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአዲስ የእዳ አፋፍ ላይ ያለችዉ አፍሪቃ

ረቡዕ፣ መጋቢት 13 2009

ወደ 40 የሚሆኑ የአፍሪቃ ሃገራት ያለባቸዉን እዳ መክፈል እንደማይችሉ ተገለጸ ። ከነዚህ ሃገራት መካከል ሞዛምቢክ በዋንኛነት የተጠቀሰች ሃገር ናት። የዶቼ ቬለዉ ዮኃንስ ቤክ የፃፈዉ ዘገባ እንደሚያሳየዉ የዛሬ አስር ዓመት ለአፍሪቃ ሃገራት የከተደረዉ የእዳ ዝረዛ በኃላ ዛሬ አፍሪቃ የዕዳ ቀዉስ አንዣቦባታል።

https://p.dw.com/p/2ZlhR
Mosambik - Metical
ምስል DW/M. Sampaio

Afrika vor einer neuen Schuldenkrise - MP3-Stereo

 

 

ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ቡድን 20 በመባል የሚታወቁት በዓለማችን በኢንዱስትሪ የበለፀጉ ሃገራትና የአደጉ ሃገራት እንዲሁም የማዕከላዊ ባንክ ዋና ተጠሪዎች የሁለት ቀን ጉባዔ በጀርመንዋ ባድን ባድን ከተማ አካሄደዋል። ጉባዔዉ መንግስታዊ ላልሆነዉ ለጀርመኑ «ኤርላስያር ዴኤ» ለተሰኘዉ ድርጅት በእዳ በመዘፈቅ ላይ ያሉ በማደግ ላይ ሃገራትን ማሳያ መድረክ እንደሚሆነዉ ገልፆአል። ድርጅቱ 40 አፍሪቃ ሃገራት ከመጠን በላይ የሆነ እዳ እንዳለባቸዉ የሚጠቁም ነገር እንዳለም ገልፆአል። «ኤርላስያር ዴኤ» የተባለዉ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት የፖለቲካ ጉዳይ አስተባባሪ ዮርገን ካይዘር እንደገለፁት በአሁኑ ወቅት የሚታየዉ የኤኮኖሚ ሁኔታ ከቀድሞዎቹ ዓመታት የእዳ ቀዉስ ጋር መመሳሰሉ የሚያስደንቅ አይደለም።

«በአሁኑ ወቅት ያለዉን የኤኮኖሚ ሁኔታ ስናጤን በ 70ዎቹና 80ዎቹ መጨረሻ የነበረዉ የ 3ተኛዉ ዓለም የእዳ ቀዉስን ስናነጻጽር ተመሳሳይነት አለዉ። በአንድ በኩል የበለፀጉት ሃገራትና ያደጉት ሃገራት የሚከፍሉት ጥቂት ወለድን ነዉ። በሌላ በኩል ደግሞ በአፍሪቃ የሚከፈለዉ ወለድ  ከ 7 እስከ 15 % መሆኑ ብርድር ለመስጠት ተፈላጊ ያደርጋታል። »

ከዚህ በተጨማሪ በአፍሪቃ ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆኑ የተፈጥሮ ጥሪ ሃብት ዋጋ መርከሱ ነዉ። ይህ ሁሉ ሃገራቱ ከፍተኛ ብድር ዉስጥ እንዲገቡ በሌላ በኩል እዳን ለመክፈል ይቸግራቸዋል ሲሉ የ «ኤርላስ ዴኤ» ድርጅት የፖለቲካ አስተባባሪ ዮርገን ካይዘር ያስጠነቅቃሉ።  በተለይ የተፈጥሮ ጥሪ ኃብት ዋጋ ሲያሽቆለቁል የነዳጅ ዘይት፤ ጋዝ፤ የድንጋይ ከስልና በሌሎች የጥሪ ኃብት ሽያጭ ላይ ጥገኛ የሆኑ ሃገራት የሚያገኙት የቀረጥ ዋጋ በመቀነሱ ኤኮኖሚያቸዉን እንደሚጎዳ ተመልክቶአል። ከጎርጎረሳዉያኑ 1996 ዓ,ም ጀምሮ በርካታ ታዳጊ ሃገራት «ከፍተኛ ብድር ያለባቸዉ ድሃ ሃገራት በሚል መርህ»  ያለባቸዉ የዕዳ መጠን በመቃለሉ አሁን የሚታየዉ የዕዳ ቀዉስ አብዛኞች የሞያዉን ገምጋሚዎች አስገርሟል።  በዚህ መረሃ ግብር  የዓለም ባንክ ፤ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም፤ የቀድሞዉ የቡድን-8 እንዲሁም ጀርመንን ጨምሮ በኢንዱስትሪ የበለፀጉት ሃገራት  ይህ እዕዳ ያመጣዉ ችግር ተቃልዋል ብሎ ያሰበ ተሳስቶአል። «ከፍተኛ ብድር ያለባቸዉ ድሃ ሃገራት« የተሰኘዉ መርህ ዘላቂነት የሌለዉ መሆኑን «ኤርላስ ዴኤ» የተሰኘዉ ድርጅት ያወጣዉ መዘርዝር ያሳያል። በመዘርዝሩ መሠረት ከ40 የአፍሪቃ ሃገራት 26 ቱ በእዳ ስረዛ መረሃ-ግብር ስር ያለፉ ናቸዉ። ከነዚህ ሃገራት መካከል ሞዛምቢክ ትጠቀሳለች።     

Infografik Schulden Mosambiks deutsch

ጋና እና ዛምብያ በከፍተኛ እዳ ዉስጥ ይገኛሉ። እንደ ሴኔጋል ያለች በብዛት የተፈጥሮ ሃብት የሌላት ሃገር ደግሞ አሁንም በእዳ ችግር ዉስጥ ተዘፍቀዋል።  ደቡብ አፍሪቃ  ከጎርጎረሳዉያኑ 2017 ዓ,ም መጀመርያ ወር ጀምሮ ያለባትን እዳ በተጠበቀዉ ጊዜ መክፈልዋን አቁማለች። ሞዛምቢክ የነዳጅ ዘይትና የድንጋይ ከሰል ኃብት የበለፀገች በመሆንዋ ባንክና መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች ገንጠባችንን አናገኝም የሚል መጠነኛ ስጋት ስላላቸዉ ብቻ በፍላጎታቸዉ ብድር  ቢሰጥዋትም በስተመጨረሻ ባዶእጃቸዉን ቀርተዋል።

« የሞዛምቢክ ሁኔታን ስናይ ለምሳሌ በጣም የተጋነነ ነዊ ሞዛምቢክ በከፍተኛ ደረጃ ዕዳ ስረዛ የተደረገላት ሃገር ናት። ጋና እና ዛምቢያም በከፍተኛ እዳ ዉስጥ ይገኛሉ። እንደ ሴኔጋል ያሉ በብዛት የተፈጥሮ ኃብት የሌላቸዉ ሃገሮች አሁንም በዕዳ ችግር ዉስጥ ተዘፍቀዋል። » ሲሉ መንግሥታዊ ያልሆነ የ«ኤርላስያር ዴኤ» ድርጅት የፖለቲካ ጉዳይ አስተባባሪ ዮርገን ካይዘር  ተናግረዋል።

የዓለም ባንክን የዕዳ መረጃ መዘርዝር የተመለከትን እንደሆነ በርካታ የአፍሪቃ ሃገራት አዲስ የኤኮኖሚ ከፍተኛ  የዕዳ ዉስጥ መግባታቸዉን ያጤናል ። ለምሳሌ ከጎርጎረሳዊዉ 2015 ዓ,ም  እስከ 2015 ዓ,ም ድረስ አንጎላ ጋና ኬንያ እና ደቡብ አፍሪቃ የብድር ዕዳ በሦስት እጥፍ ጨምሮአል። እንደ ካብቬርዴ ያሉ ትንንሽ የአፍሪቃ ሃገራትም በዚህ ጊዜ ዉስጥ አዲስ ብድርን ወስደዋል። በጉባዔዉ ላይ ለምክክር የተጋበዙ በርካታ የአፍሪቃ ሚኒስትሮች መካፈላቸው ተዘግቧል። ከአፍሪቃ ጋር በጋራ መስራት የወቅቱ የ ቡድን 20 ሊቀመንበር የጀርመን ዋንኛ ትኩረት ነዉ። 

አዜብ ታደሰ / ዮኃንስ ቤክ 

ኂሩት መለሰ