1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

ሐሙስ፣ ኅዳር 29 2009

የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ትልልቅ የግንባታ ስራዎች «በተቀመጠላቸው ጊዜ እና በጀት እንዲጠናቀቁ» እንዲሁም የግንባታ አማካሪዎች ስራቸዉን በትክክል ካልተወጡ ፍቃዳቸዉ እስከ ሶስት ዓመት እንደሚወሰድባቸዉ የሚያዝ መመሪያ ማዘጋጀቱ እየተዘገበ ይገኛል።

https://p.dw.com/p/2Ty9q
China Investment Afrika Äthiopien - AU Konferenz Center
ምስል AFP/Getty Images

New Directive for Construction - MP3-Stereo

ሚንስቴር መስርያ ቤቱ በአገርቱ የመጀመርያ የተባለዉን የኮንስትራክሸን ኦዲት የመጀመሪያ ረቂቅ መመሪያ እያዘጋጀ መሆኑን ለመረዳት ተችለዋል።

ይህ በረቂቅ ደረጃ ቢሆኒም ሌሎች ሁለት አዳዲስ መመሪያዎች፣ ማለትም በኮንስትራክሽን ፕሮጄክት የተሳታፉ የአማካሪዮች አሰራርን እና የግንባታ መሳሪያዎችን የሚመዘግብና የሚቆጣጣር መመሪያም እንደተዘጋጀ በኮንስትራክሽን ሚንስቴር የህዝብና የአለማቀፍ ግኑኝነት ፅህፈት/ቤት ምክትል ኃላፍ አቶ ስለሺ ዘገየ ለዶይቸ ቬለ ይናገራሉ።

ከአዲሶቹ መመሪያዎች በተጨማሪ መስሪያ ቤቱ በፊትም ያሉትን የዲዛይን ባለሙያዎችና አማካሪዎች ምዝገባ መመሪያ አሁን እንዳሻሻለ አቶ ስለሺ ይናገራሉ።

እነዚህ መመሪያዎች ያሰፈለጉበት  ምክንያት፣  የተቀመጡት ግንባታዎች በተመደበላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጨርሱ፣ በተሰጣቸው በጀት እንዲሁም የወጡትን የግንባታ ጥራት ደንቦች ለማስጠበቅ እንደሆነም የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግቦታል። የመመሪያዉ ተፈፃሚነት በግንባታ ዘርፍ የሚሳተፉ የመንግስትም ሆነ የግል ላይ መሆኑን አቶ ስለሺሲሌሽ ይናገራሉ።

የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በዘገባቸዉ የግንባታ አማካሪዎች «ስራቸውን በአግባቡ ካልተወጡ የካሳ ክፍያ ጨምሮ ከሁለት እስከ ሶስት ዓመት የሚደርስ የሙያ ፈቃድ እገዳ» እንደሚጣልባቸዉና በዲዛይን ባለሙያዎችና አማካሪዎች ምዝገባ መመሪያ እንደሚታይ ጠቅሰዋል።

መርጋ ዮናስ

አረያም ተክሌ